August 2, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ሲዳማ ቡና የኢትዮጵያ ዋንጫ ሻምፒዮን ሆነ

ማሻ ፣ የሰኔ 01፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) በኢትዮጵያ ዋንጫ ፍጻሜ ሲዳማ ቡና ወላይታ ድቻን 2 ለ 1 በማሸነፍ ሻምፒዮን ሆኗል።

በአዲስ አበባ ስቴዲየም በተደረገው ጨዋታ ሀብታሙ ታደሰ እና የቀድሞው የኢትዮጵያ ቡና አጥቂ መስፍን ታፈሰ የሲዳማ ቡናን ግቦች አስቆጥረዋል።

በዝግ ስቴዲየም በተደረገው የፍጻሜ ጨዋታ ካርሎስ ዳምጠው የወላይታ ድቻን ብቸኛ ግብ ያስገኘ ተጫዋች ሆኗል።

ሲዳማ ቡና የኢትዮጵያ ዋንጫን ማንሳቱን ተከትሎ በታሪኩ ለመጀመርያ ጊዜ በቀጣይ አመት በካፍ ኮንፌደሬሽን ዋንጫ ኢትዮጵያን የሚወክልም ይሆናል።

ወላይታ ድቻ በ2ኛው አጋማሽ ከተደጋጋሚ ሙከራዎች ባሻገር ግብ ቢያስቆጥርም ከጨዋታ ውጭ በሚል ተሽሮበታል።

በ2010 ዓ.ም በተሳተፈበት የኮንፌደሬሽን ዋንጫ በ1ኛው ዙር ቅድመ ማጣሪያ የግብጹን ጠንካራ ክለብ ዛማሊክ በደርሶ መልስ አሸንፎ የነበረው ወላይታ ድቻ በድጋሜ በአፍሪካ መድረክ የሚሳተፍበትን ዕድል ሳይጠቀምበት ቀርቷል።

የኢትዮጵያ ዋንጫ ከአራት አመታት መቋረጥ በኋላ በ2016 ዓ.ም መጀመሩም ይታወሳል።

ደ/ሬ/ቴ/ድ