ማሻ ፣ የግንቦት 19፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ልማትና በኮንስትራክሽን ዘርፍ በርካታ የሥራ ዕድል እየፈጠረች መሆኗ የሚደነቅ ነው ሲሉ የዓለም ሥራ ድርጅት የሥራ፣ ልማትና ኢንቨስትመንት ክፍል ሃላፊ ሚቶ ትሱካሞቶ ገለጹ፡፡
ኢትዮጵያ 20ኛውን የዓለም ሥራ ድርጅት ቀጣናዊ ስብሰባ በብቃት በማስተናገድ በታዳሚዎች ዘንድ እውቅና ተችሯታል፡፡
በአዲስ አበባ የተገነቡ የአረንጓዴ ልማት፣የቱሪዝም ስፍራዎች፣ ኢንዱስትሪ ፓርኮችና የኮሪደር ልማት ፕሮጀክቶችን በመጎብኘት ኢትዮጵያ የሥራ ዕድል ፈጠራና ዘላቂ ልማት ትኩረት መስጠቷን አረጋግጠዋል፡፡
የዓለም ሥራ ድርጅት የሥራ፣ ልማትና ኢንቨስትመንት ክፍል ሃላፊ ሚቶ ትሱካሞቶ ለኢዜአ እንዳሉት፤ በአዲስ አበባ የተጀመረው የኮንስትራክሽን ዘርፍ በርካታ የሥራ እድል መፍጠሩን የሚደነቅ ነው፡፡
ወደ አዲስ አበባ የመጣሁት ከስምንት ዓመት በፊት ኢትዮጵያ 17ኛው የዓለም የሥራ ድርጅት አህጉራዊ ስብሰባ ስታስተናግድ ነበር ያሉት ሃላፊዋ፤ አሁን አስደናቂ ለውጦችን መመልከታቸውን ገልጸዋል፡፡
በአዲስ አበባ በርካታ የተገነቡና በመገንባት ላይ ያሉ ፕሮጀክቶች መኖራቸውን ገልጸው፤ የኮንስትራክሽን ስራዎች ኢንቨስትመንትን በመሳብ ሰፊ የሥራ ዕድል እየፈጠሩ ነው ብለዋል፡፡
የመሰረተ ልማት ዝርጋት ከፍተኛ የሆነ የሥራ ዕድል የመፍጠር አቅም እንዳለው የገለጹት ሃላፊዋ፥ኢትዮጵያ አረንጓዴ ከተሞችን የመገንባት ሂደት ላይ መሆኗን ተረድቻለሁ ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ የዓለም ሥራ ድርጅት የሥራ ዕድል በሚፈጥሩ የመሰረተ ልማት ዘርፍ ላይ ለተሰማሩ ሀገራት የሚያደርገው ድጋፍ ተጠቃሚ እንደሆነች ገልጸዋል፡፡
የኮንስትራክሽን ሥራዎች የአካበባው ማህበረሰብ በባለቤትነት እንዲሳተፍበት የሚያደርግ መሆኑን በማንሳት፤ በኢትዮጵያ በተለይም በአዲስ አበባ የተመለከትኩት ይሄን ነው ብለዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡
More Stories
ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከዳያስፖራው ማህበረሰብ አጀንዳ ማሰባሰብ ጀመረ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት የዘርፍ ቋሚ ኮሚቴዎች የ2017 በጀት አመት የአስፈፃሚ አካላት አፈፃፀም ግምገማ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
ማህበረሰቡ በከባድ ዝናብ ምክንያት ከሚከሰቱ አደጋዎች እንዲጠነቀቅ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አሳሰበ።