ማሻ ፣ የግንቦት 19፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) “ሀገር እና ጥበብ፦ጥበብ ለኢትዮጵያ ማንሰራራት” በሚል መሪ ቃል ከኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ጋር በሸካ ዞን ማሻ ከተማ የውይይት መድረክ ተካሄደ።
የውይይት ሰነዱን ያቀረቡት የሸካ ዞን ባህል ቱርዝምና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ጀመረ ተሰማ የኪነ ጥበብ ሰዎች አከባቢያቸውንና ሀገራቸውን ከማስተዋወቅ ረገድ ድርሻቸው ከፍተኛ እንደሆነ አንስተዋል።
የተለያዩ ጥበብ ያላቸውን ግለሰቦች ዕውቀታቸውን ከመጠቀም አንፃ ክፍተት በመኖሩ የምርምር ስራዎችን በመስራት ችግሮችን መለየት ያስፈልጋል ስሉ አቶ ጀመረ ተናግረዋል።
ከቅርብ አመታት ወዲህ በተለያዩ ማህበራዊ ገጾች የምተላለፉ የጥበብ ስራዎች ልበረታቱ እንደምገባና በአከባቢያችን ያሉ የኪነ ጥበብና የዕደ ጥበብ ሰዎችን አለመደገፍ፣ ያለንን ጥበብ አውተን አለመጠቀም፣ተተኪ አለማፍራት፣ለሙያው ያለን አመለካከት አናሳ መሆንና መድረኩ በጥበቡ አለም ላሉት ተስፋ መሆኑ ከተሳታፍዎች ተነስቷል።
የውይይት መድረኩን የመሩት የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ በበኩላቸው ጥበብን በአግባቡ ስንጠቀም ለሀገር እድገት ጠቀሜታ እንዳለው ሁሉ በአግባቡ ካልተጠቀምን ሀገርን ስለምያፈርስ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።
ከመድረኩ ለተነሰቡ ሀሳብና አስተያየቶች በምመለከታቸው አካላት ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶ ውይይቱ ተጠናቋል።
በውይይቱ የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ፣ የሸካ ዞን ባህል ቱርዝም ስፓርት መምሪያ ኃላፍ አቶ ጀመረ ተሰማ፣የዘርፉ ባለሙያዎች፣ተጋባዥ እንግዶች እና የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ተገኝተዋል።
በልጃለም ማሞ
More Stories
ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከዳያስፖራው ማህበረሰብ አጀንዳ ማሰባሰብ ጀመረ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት የዘርፍ ቋሚ ኮሚቴዎች የ2017 በጀት አመት የአስፈፃሚ አካላት አፈፃፀም ግምገማ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
ማህበረሰቡ በከባድ ዝናብ ምክንያት ከሚከሰቱ አደጋዎች እንዲጠነቀቅ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አሳሰበ።