ማሻ ፣ የግንቦት 20፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) የኬንያ ህገ አውጪ ምክር ቤት የኢጋድን ስምምነት ማፅደቁን የምስራቅ አፍሪካ በየነ መንግሥታት የልማት ድርጅት (ኢጋድ) ዋና ፀሃፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) አድንቀዋል።
የኢጋድ ስምምነት በሀገሪቱ ምክር ቤቱ መፅደቁ ድንበር ዘለለ ተግዳሮቶችን በመከላከል ዘላቂ ሰላምንና ብልፅግናን ለማረጋገጥ ቀጠናዊ ትብብርና ለማጠናከር ያግዛል ብለዋል።
የቀጠናው ሀገራት በጋራ ጉዳይ ለመስራት ቁርጠኝነታቸውን የሚገልፁበት የኢጋድ ስምምነት ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ በጅቡቲ እና በደቡብ ሱዳን ህግ አወጪ አካላት መፅደቁ ይታወሳል።
በሀገራቱ መካከል ሰላማዊ ግንኙነትን ማረጋገጥ፣ ጤናማ ጉርብትና መፍጠር፣ በጎረቤት ሀገራት ጉዳይ ጣልቃ አለመግባት፣ በሀገራቱ መካከልም ሆነ በሀገራቱ ውስጥ የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን በሰላማዊ መንገድ መፍታት፣ ቀጠናቂ ሰላምን መረጋጋት እንዲሁም ደህንነት ማረጋገጥ የኢጋድ ስምምነት ዋንኛ ዓላማዎች ናቸው ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።
More Stories
በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ቴፒ ግቢ አዘጋጅነት የተካሄደው14ኛው ሀገር አቀፍ የምርምር ጉባኤ ተጠናቀቀ ።
ማዕከሉ ከተቋቋመ አጭር ጊዜ ውስጥ 21ሺ 5መቶ ቶን በላይ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ማቅረቡን በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የቴፒ ምርት ጥራት ምርምርና ሰርትፍኬሽን ማዕከል አስታወቀ።
አሜሪካ ከኢራን ጋር ባደረገችው ጦርነት 25 ቢሊየን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ አጣች