ማሻ ፣ የግንቦት 13፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) 45ኛ መደበኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብስባ ውሳኔዎች
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት በቨርቹዋል ባካሄደው 45ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡
1. በቅድሚያ ምክር ቤቱ የተወያየው የባለብዙ ተዋንያን የግብርና ኤክስቴንሽን አገልግሎትና አስተዳደር ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡ በሀገራችን ባለፉት ዓመታት የግብርና ኤክስቴንሽን አገልግሎት በመንግሥት ብቻ ሲሰጥ ቆይቷል፡፡
እያደገ ከመጣው የዘርፉ ፍላጎት አንፃር መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን፣ የግል ዘርፉን፣ የሕብረት ሥራ ማሕበራትንና የሙያ ማሕበራትን ማሳተፍ የሚያስችል የአሰራር ሥርዓት መዘርጋት ያስፈልጋል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
2. በመቀጠል ምክር ቤቱ የተወያየው የሥርዓተ ምህዳር አገልግሎት ክፍያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡ በሀገራችን የሥርዓተ ምህዳር ክፍያ አሰራርን የተመለከተ የህግ ማዕቀፍ ባለመኖሩ ወጥ ባልሆነ አሰራር በተለያዩ አካላት ሲተገበር ቆይቷል፡፡
አሁን በደረስንበት የእድገት ደረጃ የፌዴራል እና የክልል ተቋማት፣ የግሉ ዘርፍ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ከግምት ውስጥ ያስገባ የህግ ማዕቀፍ መኖር አስፈላጊ ይሆናል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
More Stories
አቶ አንዱአለም ጌታቸው የማሻ ከተማ ከንቲባ ሆነው ተሾሙ፡፡
ኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብርን ያለማቋረጥ በመተግበር ምሳሌ ሆናለች – ገመዶ ዳሌ (ዶ/ር)
በተገባደደዉ የበልግ አዝመራ ከ9 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ የእንሰት ችግኝ መትከሉን የአንድራቻ ወረዳ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ፅ/ቤት አስታወቀ ።