ማሻ ፣ የግንቦት 11፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) በስደት፣ መፈናቀል እና ከተማኔነት ላይ ያዘጋጀው 4ኛው የሳይንስ ጉባዔ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።
ጉባዔው “ስደት፣ መፈናቀል እና ከተሜነት በዘላቂ ልማት ላይ ያላቸው ተጽዕኖ” በሚል መሪ ሀሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኘው።
በመድረኩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምሁራን፣ ተመራማሪዎች፣ ፖሊሲ አውጪዎች፣ ከንቲባዎች፣ የልማት ባለሙያዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
በጉባዔው የስደትና መፈናቀል ምክንያቶችን በመፈተሽ በእውቀትና ተጨባጭ መረጃ ላይ የተመሰረቱ የመፍትሄ አቅጣጫዎች እንደሚቀመጡ ተመላክቷል፡፡
የስደተኞች እና ተመላሾች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ጠይባ ሀሰን÷ የኢትዮጵያን ውጤታማ የስደተኞች አያያዝ እና አገልግሎት ተሞክሮ አቅርበዋል።
የኢጋድ የኢትዮጵያ ተጠሪ አቶ አበባው ቢሆነኝ በበኩላቸው÷ በቀጣናው የከተማ እድገት ያመጣቸው ፈተናዎች የተቀናጀ እና መረጃን መሰረት ያደረገ ምላሽ እንደሚያሻቸው ገልጸዋል።
ዜጎች በኢጋድ ቀጣና የሚያደርጉት እንቅስቃሴ በከተሞች እድገት፣ ኢኮኖሚ እና ማህበራዊ መስተጋብር ላይ ጫና እያሳደረ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
በቀጣነው የስደተኞችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተከናወኑ ላሉ ሥራዎች ኢጋድ እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል፡፡
ፋና
More Stories
በተገባደደዉ የበልግ አዝመራ ከ9 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ የእንሰት ችግኝ መትከሉን የአንድራቻ ወረዳ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ፅ/ቤት አስታወቀ ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ስለዲጅታል ማንነት ያስተላለፉት መልዕክት፦
አዳዲስ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ወደ ስራ መግባታቸው ለኮንስትራክሽን ዘርፉ ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል ተባለ።