ማሻ ፣ የግንቦት 06፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) ከተረጂነት ወደ ምርታማት በመሸጋገር የተሟላ ሃገራዊ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ከሁሉም የብልጽግና አባላት እንደሚጠበቅ ተገልጿል።
ከተረጂነት ወደ ምርታማት ወደ ተሟላ ሃገራዊ ሉዓላዊነት በሚል መሪ ሀሳብ ቅጽ 1 ቁጥር 6 የልሳነ ብልጽግና ንድፈ ሀሳብ መጽሔት ላይ ከአባላት ጋር ውይይት ተደርጓል።
የመወያያ ሰነዱን ያቀረቡት የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ የሺዋስ ዓለሙ ከተረጂነት ወደ ምርታማት በመሸጋገር የተሟላ ሃገራዊ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ከሁሉም የብልጽግና አባላት እንደሚጠበቅ አስረድተዋል ።
የክልል ማዕከል አስተዳደር የብልጽግና ህብረት አመራሮችና የብልጽግና ቤተሰብ አባላት በተሳተፉበት በቀረበው የመወያያ ሰነድ ምርታማነትን በማሳደግ የተሟላ ሀገራዊ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ጥገኛ ከሆነ አስተሳሰብ ፈጥኖ መውጣት ይገባል ብለዋል።
በልሳነ ብልጽግና ንድፈ ሀሳብ መጽሔት ሀገራዊ ቁመናን፣ እሳቤያዊና አሁናዊ ሁኔታ እንዲሁም አስቻይ ሁኔታዎች እና ማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርምና አንድምታው በተሰኙ ወሳኝ ርዕሶች ላይ ገለጻ አድርገዋል ሲል የክልሉ ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።
More Stories
ምክር ቤቱ አራት ስምምነቶችን አጸደቀ
ለውጭ ባለሀብቶች ዝግ ሆነው የቆዩ ዘርፎች መከፈት የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን እያሳደገ ነው
3ኛው ዓለም አቀፍ የሰላም፣ የአብሮነትና የልማት ጉባኤ ነገ መካሄድ ይጀምራል