May 12, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

54ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ተጠናቀቀ

ማሻ ፣ የግንቦት 03፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ሲካሄድ የቆየው 54ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በድምር ውጤት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሸናፊነት ተጠናቅቋል።

በሻምፒዮናው በድምር ውጤት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ279 ነጥብ አንደኛ ደረጃን ይዞ ሲያጠናቅቅ፣ መቻል በ242 ነጥብ ሁለተኛ እንዲሁም ሸገር ሲቲ በ143 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቀዋል።

በሻምፒዮናው 1 ሺህ 379 አትሌቶች፣ 31 ክለቦችና ተቋማት እንዲሁም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ተሳትፈዋል።

በሻምፒዮናው ማጠቃለያ ሥነ ሥርዓት ላይ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዲኤታ ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህንን ጨምሮ የፌደሬሽኑ አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ፋና