በቀድሞ የደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ስር የነበሩ የካፋ፣ የዳውሮ፣ የቤንች ሸኮ፣ የሸካና የምዕራብ ኦሞ ዞኖች እና የኮንታ ልዩ ወረዳ ህዝቦች የዘመናት በክልል የመደራጀት ጥያቄ የብልፅግና ፓርቲ በሚመራው የለውጡ መንግስት ምላሽ በማግኘቱ በህዳር 14/2014 ዓ.ም የፌደሬሽኑ 11ኛ ክልል ሆኖ የተመሠረተ ክልል ነው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል፡፡
ክልሉ የኮንታ ልዩ ወረዳ ህዝቦችን በዞን የመደራጀት የዘመናት ጥያቄ ወዲያውኑ በመመለስ ስድስት ዞኖችን አቅፎ የተደራጀ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት 20 የከተማ አስተዳደሮች፣ 41 የወረዳ አስተዳደሮች፣ 806 የገጠር ቀበሌ አስተዳደሮችና 122 የከተማ ቀበሌ አስተዳደሮች (በድምሩ 928 ቀበሌዎች) ያሉት ነው፡፡
More Stories
በኢትዮጵያ #ገና ለምን ታህሳስ 29 ይከበራል?
ታህሳስ 04/2017 ዓ.ም የዕለተ ዓርብ ጠዋት ስርጭት፡፡
“የመሻገር ጥሪቶች፤ የአዲስ ብርሃን ወረቶች”