May 1, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

በገጠሩ የሀገሪቱ አካባቢዎች መንግስት የሚዘረጋቸውን የተለያዩ ኢንሸቲቦችን ቀድሞና ፈጥኖ ተግባራዊ ከማድረግ አንፃር የተሻሉ አፈጻጸሞች መታየታቸው ተገለፀ ።

ማሻ ፣ የሚያዝያ 23፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) በሸካ ዞን ማሻ ወረዳ የካንጋ ቀበሌ አርሶ አደሮች የኮርደር ስራ ጥቅሙን በመረዳት ትኩረት ሰጥቶ እየሰሩ ይገኛሉ።

የካንጋ ቀበሌ ሞዴል አርሶ አደር አመነ አምበሎ እንደሚሉት የቤትና ግቢውን ውቤት ለመኖሪያ ጽዱና ሚቹ አደረገው መኖር ከአባቶቻችን የወረስነው ባህላችን ቢሆንም አሁን መንግስት በሰጠው ትኩረትም ደስተኛ መሆናቸውን ይናገራሉ።

የቀለም ትምህርትን እስከ 7ተኛ ክፍል እንደተማሩ የሚናገሩት ሞዴል አርሶ አደሩ ከ6 በላይ ልጆችን በማስተማር ለተለያዩ መንግስት ስራ በማድረስ ባላቸው ዕውቀትና ትጋት ጽዱና ሚቹ አካባቢን ከመፍጠር በላይ በጊቢያቸው ዙሪያ እንሰት፣ጎመንና ፍራፍሬ በማዘጋጀት የተትረፈረፈ ማዕድ እንዳላቸው ይገልጻሉ።

ለስራቸው ስኬት ባለቤቶቻቸውና የልጆቻቸው ድጋፍ ከፍተኛ መሆኑንና መንግስት ለዚሁ ስራ እያደረገ ላለው ልዩ ትኩረት ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።

ለሌሎች ሰዎችም ተሞክሯቸውንና ልማዳቸውን በማካፈል ውብና ሚቹ አካባቢ እንድፈጥሩ በትኩረት እንደሚሰሩ ሞዴል አርሶ አደሩ አልሸሸጉም።

በሁለገብ ተግባራቸውና በታታሪነታቸው የሚታወቁ አርሶአደር አመነ አምበሎ አዳዲስ ስራን ለአካባቢው ከማሳየት አልፎ የመንግስት ትኩረት አቅጣጫን ቀድሞ በመረዳት ተግባራዊ የሚያደርጉ ሞዴል አርሶ አደር መሆናቸውን ምስክርነት የሰጡት ጎረበትና የቀበሌው አስተዳዳሪ አቶ አየለ አዴሞ ልምዳቸውን ለሌሎች በማጋራት አብሮ ማደግና መለወጥን የሚሹ ጠንካራ ሰው መሆናቸውን ገልጸዋል።