ማሻ ፣ የሚያዝያ 23፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) በሸካ ዞን ማሻ ወረዳ ወሎ ሾባ ቀበሌ በሻይ ምርት አውትግሮውርስ በ2010 ዓ ም ከ30 በላይ ወጣቶች የአብ ስራ በሚል ስያሜ ተደራጅተው 17ነጥብ 5 ሄክታር ከመንግስት አገኝተው ወደስራ መግባታቸውን ይናገራሉ።
ከዚህም 10 ሄክታር በማልማት ለቀሪው ስፊ ዝግጅት እያረግነው ሲሉ የማህበሩ ሰብሳቢ ትግሉ አበራና የማህበሩ ጸሐፊ ወጣት መስፍን አየለ ገልጸዋል።
በክረምንት በወር ሁለት ጊዜ በበጋ አንድ ጊዜ ምርት የሚሰጥ መሆኑን የተናገሩት አባላቱ በአንድ ጊዜ 10 ሺህ ኪሎ ግራም እንደሚያገኙ ያብራራሉ።
ስራው ውጤታማ መሆኑን የሚገልጹት ወጣቶቹ ከእራሳቸው አልፎ ለበርካታ ሰዎች የስራ ዕድል እንደፈጠሩም ይናገራሉ።
የተለያዩ ግብዓት፣ የክሂሎት ክፍተትና የገቢያ ትስስር ካለመጠናከሩ የተነሳ 1ኪሎ ግራም ምርትን በ4ብር እየሸጥን ነው ያሉት ወጣቶች ችግሩን የሚመለከተው አካል እንድቀርፍልን ሲሉ ጠይቀዋል።
የማሻ ወረዳ ግብርና ደን አካባቢና ህብረት ስራ ጽህፈት ቤት ምክትል ኃላፊና የእርሻና ህብረት ስራ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ታመነ ከበደ በወረዳው በግልና በማህበር ተደራጅተው በሻይ ምርት አውትግሮውርስ የገቡት በርካቶች መሆናቸውን ገልጸው ከነዚህም ዋናውና ሞዴል የነዚህ ወጣቶች ነው ብለዋል።
የወጣቶቹን የክሂሎት ክፍተትን ለመሙላት በቅርቡ ስልጠና ለመስጠት ዝግጅት ማጠናቀቃቸውንና የገቢያ ትስስርና ዋጋን በሚመለከት ከኢስት አፍርካ አግሮ ኢንዱስትሪ ጨዋቃ ሻይ ልማት ጋር እየተነጋገሩ መሆናቸውን ኃላፊው ተናግረዋል።
More Stories
ማህበረሰቡ በከባድ ዝናብ ምክንያት ከሚከሰቱ አደጋዎች እንዲጠነቀቅ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አሳሰበ።
የሰው ተኮር ተግባራት በማጠናከር ሁለተናዊ ዕድገትን ለማረጋገጥ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ ገለፁ።
የህዳሴው ግድብ መጠናቀቅ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ትስስርን ያሳድጋል