ማሻ ፣ የመጋቢት 16፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም ) የሸካ ዞን አስተዳደር ምክር ቤት የ6 ወር አፈጻጸም ሪፖርት በዝርዝር ለምክር ቤቱ አባላት ቀርበዋል።
የተፈጥሮ ሀብት ደንና አካባቢ ጥበቃ ዘርፍ የተፈሳስ ዕቅድ 15 ሺህ 1መቶ 76 ሄክታር ሲሆን ክንውን አዲስ 5 ሺህ 1መቶ 44 ሄክታር ነባር ደግሞ ከ10 ሺህ ሄክታር በመሆኑ በአጠቃላይ 14 ሺህ 8መቶ 72 መከናወኑ በሪፖርቱ ቀርበዋል።
በሥነ ህይወታዊ ልማት አፈጻጸም በ2016/2017 ዓ ም በተደረገው የጽድቀት ቆጠራ ከተተከለው 11 ሚሊየን 1መቶ 93 ሺህ 9 መቶ 79 ችግኝ ውስጥ 9 ሚሊየን 5 መቶ 82 ሺህ 46 የጸደቀ ሲሆን የጸደቀ ሲሆን የጽድቀት መጠኑ 85 ነጥብ ፐርሰንት መሆኑ ተገልጸዋል።
ከአርንጓዴ አሻራ መረሐ ግብር ፤የአነስተኛ መስኖ ልማት፤ የአፈር ለምነት ማሻሻያ ስራ፤ የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም፤በመንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ይዞታ መለካት፤ አካባቢ ጥበቃና አየር ንብረት ለውጥ አፈጻጸም፤ ደን ልማትና ብዘሃ ልማት ስራን በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ዋና አስተዳዳሪ በሪፖርታቸው አብራርተዋል።
የREED+ ኢንቨስትመንት ኘሮግራም አፈጻጸም ህብረት ስራን በማደራጀትና በማጠናከር በዞኑ በሦስት ወረዳዎች አሳታፊ የደን አስተዳደር ማህበራትን በመመስረት ጠንካራ ድጋፍና ክትትል ተደርገው በትኩረት እየተሰራ እንዳለ ዋና አስተዳዳሪ ተናግረዋል።
More Stories
ማህበረሰቡ በከባድ ዝናብ ምክንያት ከሚከሰቱ አደጋዎች እንዲጠነቀቅ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አሳሰበ።
የሰው ተኮር ተግባራት በማጠናከር ሁለተናዊ ዕድገትን ለማረጋገጥ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ ገለፁ።
የህዳሴው ግድብ መጠናቀቅ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ትስስርን ያሳድጋል