ማሻ ፣ የመጋቢት 03 ፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም ) የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የ1446 ዓ.ሂ ወይም የ2017 ዓ.ም የሐጅ ጉዞ እና ሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ሰጥቷል።
የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ በዚሁ ወቅት፥ የዘንድሮው የሐጅ ጉዞ ምዝገባ በሳውዲ ሐጅ ሚኒስቴር መመሪያና ፈቃድ መሠረት የሚካሄድ መሆኑን ጠቅሰው፤ ምዝገባው እስከ ረመዷን 29 (መጋቢት 20) ድረስ መራዘሙን ገልፀዋል።
በዘንድሮው የሐጅ ጉዞ 10 ሺህ ሑጃጆችን ለማሳተፍ መታቀዱን ጠቅሰው፤ ምዝገባው በሀገሪቱ ዙሪያ በሚገኙ 30 የምዝገባ ጣቢያዎች በቴክኖሎጂ ታግዞ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።
የሐጅ ጉዞ ምዝገባው እስከ መጋቢት 20/2017 ዓ.ም ድረስ መራዘሙን በማብሰር በዚህ ዓመት ሐጅ ለማድረግ አቅሙና ፍላጎቱ ያላቸው ምዕመናን በአቅራቢያቸው ባሉ የምዝገባ ጣቢያዎች ተገኝተው እንዲመዘገቡ ጥሪ አቅርበዋል።
ኢቢሲ
More Stories
በቀጣዮቹ ቀናት በበርካታ አካባቢዎች የክረምቱ ዝናብ ተጠናክሮ ይቀጥላል
በአዕምሮ የበለጸገ ትውልድ እንዲፈጠር የምግብ -ስርዓትና ስርዓተ – ምግብ ትግበራዎችን በቅንጅት መምራት እንደሚገባ ተገለጸ
267ኛው የሮማ ካቶሊክ ሊቀ ጳጳስ መመረጡን አስመልክቶ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የተሰበሰቡ ምዕመናን ደስታቸውን ሲገልፁ