በቢሊየነሩ ኤሎን መስክ የሚመራ ቡድን ኦፕን ኤ.አይ የተባለውን የሰው ሰራሽ አስተውሎት አበልጻጊ ድርጅት በ97 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር ለመግዛት ማቀዳቸው ተሰማ።
መስክ ኦፕን ኤ.አይ ትርፋማ ኩባንያ ለመሆን የሚያደርገውን ሽግግር ለመግታት ነው ድርጅቱን ለመግዛት ጥሪ ያቀረበው ተብሏል።
በፈረንጆቹ 2015 ኦፕን ኤአይን ከአሁኑ የድርጅቱ ባለቤት ሳም አልትማን ጋር በጋራ ያቋቋመው መስክ ብዙም ሳይቆይ ድርጅቱን ለቆ መውጣቱ ይታወቃል።
ሰው ሰረሽ አስተውሎት (ኤ.አይ) ደህንነት የተጠበቀ እና ለተጠቃሚዎች ነጻ መሆን እንዳለበት የሚያምነው መስክ በጨረታ በቡድኑ አማካኝነት ድርጅቱን በ97 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር ለመግዛት ዝግጁ መሆኑን አስታውቋል።
መስክ ያቀረበው ድርጅቱን የመግዛት ጥያቄ ያላስደሰተው የኦፕን ኤ.አይ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሳም አልትማን “ለጥያቄህ እናመሰግናለን አንሸጥልህም ከፈለክ ግን ትዊተርን በ9 ነጥብ 74 ቢሊዮን ዶላር ልንገዛህ እንችላለን” ሲል በኤክስ ባሰፈረው መልእክት ቀልዶበታል።
የኦፕን ኤአይ የቦርድ አባላትም ጥያቄውን ውድቅ ማድረጋቸን ሮይተርስ ዘግቧል።
ሳም አልትማን ኦፕን ኤ.አይን ተርፋማ ድርጅት ለማድረግ፣ አዳዲስ ሰው ሰራሽ አስተውሎት ሞዴሎችን ለመፍጠር እና ኢንቨስተሮችን ለመሳብ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ነው።
ባለፈው ወር ዲፕሲክ የተባለው የቻይና ሰው ሰራሽ አስተውሎት በትንሽ ወጭ፣ በውስን የሰው ኃይል ተገዳዳሪ የሆነ ምርት ይፋ ማድረጉን ተከትሎ እንደ ኦፕን ኤ.አይ.፣ ጉግልና ሜታ በመሳሰሉ የአሜሪካ ሰው ሰረሽ አስተውሎት አበልጻጊ ኩባንያዎች ሰፈር ድግጋጤ መፍጠሩ ይታወሳል።
More Stories
ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከዳያስፖራው ማህበረሰብ አጀንዳ ማሰባሰብ ጀመረ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት የዘርፍ ቋሚ ኮሚቴዎች የ2017 በጀት አመት የአስፈፃሚ አካላት አፈፃፀም ግምገማ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
ማህበረሰቡ በከባድ ዝናብ ምክንያት ከሚከሰቱ አደጋዎች እንዲጠነቀቅ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አሳሰበ።