የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዞች ክልል ትምህርት ቢሮ ጋር በጋራ በመሆን በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ ከአንደኛና ከቅድሜ አደኛ ደረጃ ለተወጣጡ ለ1መቶ28 መምህራን የአቅም ግንባታ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።
የሸካ ዞን ትምህርት ቢሮ መምሪያ ኃላፊ አቶ መስፍን አለሙ እንደገለፁት ሥልጠና ከክልሉ ትምህርት ቢሮ ጋር በጋራ በመሆን ለ1መቶ28 መምህራን ለአንደኛና ለቅድሜ አንደኛ ደረጃ እየተሰጠ መሆኑን ገልፀዋል።
እየተሰጠ ያለው ሥልጠና የማስተማር ስነ ዘዴ ላይ፣ የአቅም ግንባታ ደረጃ ማሻሻልና የሙያ ብቃት ሚዘና ላይ እየተሰጠ መሆኑንና አዲሱ ስረዓተ ትምህርት ጋር ተያይዞ ተማሪዎች በዕውቀትና በክህሎት ታንፀው ከስራ ጠባቅነት ስራ ፈጣር እንዲሆኑ የተዘጋጀ መሆኑን ገልፀዋል።
ሰልጣኞች በበኩላቸው እየተሰጠ ያለው ስልጠና የተሻለ አቅም የሚገነባ መሆኑን ገልፀው እየሰለጠኑ ባሉት ስልጠና ለቀጣይ ለመማር ማስተማር ብቁ መምህር ብቁ ትውልድ እንድቀርፅ ስልጠናው ተገቢ መሆኑን ተናግረዋል።
የመጀመሪያ ዙሪ ስልጠና ከአምስቱ መዋቅሮች ለተወጣጡ መምህራን ለተከታታይ አምስት ቀናት እንደሚቀጥል ተገልጿል
More Stories
ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከዳያስፖራው ማህበረሰብ አጀንዳ ማሰባሰብ ጀመረ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት የዘርፍ ቋሚ ኮሚቴዎች የ2017 በጀት አመት የአስፈፃሚ አካላት አፈፃፀም ግምገማ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
ማህበረሰቡ በከባድ ዝናብ ምክንያት ከሚከሰቱ አደጋዎች እንዲጠነቀቅ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አሳሰበ።