ኢትዮጵያ እና ሳውዲ አረቢያ በተለያዩ ዘርፎች ያላቸውን ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ ተስማምተዋል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከሳዑዲ አረቢያ የውጭ ጉዳይ ምክትል ሚኒስትር ኢ/ር ዋሊድ አብዱልከሪም አልኩራይጂ ጋር በሪያድ ምክክር አድርገዋል። ሁለቱ ወገኖች በተለያዩ ዘርፎች ያላቸውን ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ እና በሁለትዮሽ እና በአለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ውጤታማ ትብብር በማድረግ የጋራ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ተስማምተዋል። በውይይቱ ሁለቱም ወገኖች የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር እና ረቂቅ ስምምነቶችን ተግባራዊ ለማድረግ በጋራ ለመስራት መስማማታቸውንም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል
#EBC
More Stories
በቀጣዮቹ ቀናት በበርካታ አካባቢዎች የክረምቱ ዝናብ ተጠናክሮ ይቀጥላል
በአዕምሮ የበለጸገ ትውልድ እንዲፈጠር የምግብ -ስርዓትና ስርዓተ – ምግብ ትግበራዎችን በቅንጅት መምራት እንደሚገባ ተገለጸ
267ኛው የሮማ ካቶሊክ ሊቀ ጳጳስ መመረጡን አስመልክቶ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የተሰበሰቡ ምዕመናን ደስታቸውን ሲገልፁ