አቶ አቶም በክልሉ ሕዝቦች የነፃነት ትግል ውስጥ እጅግ ውድ የሆነ ዋጋ ከከፈሉ የነፃነት ዓርበኞች መካከል በቀዳሚነት የሚጠቀሱ መሆናቸውን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አሻድሊ ሀሰን ገልጸዋል፡፡አቶ አሻድሊ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት የሐዘን መግለጫ መልዕክት÷ አቶ አቶም ዕድሜ ዘመናቸውን ለክልሉ ሠላምና ልማት ሲታትሩ የኖሩ ባለ ራዕይ መሪ ነበሩ ብለዋል፡፡ሠላምና መረጋጋትን ለመፍጠር ያበረከቱት አስተዋፅዖ በክልሉ ሕዝብ ታሪክ ውስጥ የላቀ ስፍራ የሚሰጠውና ሲወሳ የሚኖር መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመጀመሪያው ርዕሰ መሥተዳድርና የነፃነት ትግል ዓርበኛ የነበሩት አቶም ሙስጦፋ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡

More Stories
ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከዳያስፖራው ማህበረሰብ አጀንዳ ማሰባሰብ ጀመረ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት የዘርፍ ቋሚ ኮሚቴዎች የ2017 በጀት አመት የአስፈፃሚ አካላት አፈፃፀም ግምገማ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
ማህበረሰቡ በከባድ ዝናብ ምክንያት ከሚከሰቱ አደጋዎች እንዲጠነቀቅ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አሳሰበ።