የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች የተገነቡ 837 መኖሪያ ቤቶችን ለአቅመ ደካሞች እና ለሀገር ባለውለታ ነዋሪዎች አስተላልፈዋል።
ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው፤ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተገንብተው ለነዋሪዎች ከተላለፉ ቤቶች ውስጥ የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር በየካ ክፍለ ከተማ 54 ቤቶችን የገነባ ሲሆን ለዚህም ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚልን አመሰግናለሁ ብለዋል።
እንዲሁም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለከተማ በተለያዩ ባለሀብቶች 108 ቤቶች፣ በአራዳ ክፍለ ከተማ በአብዱለጢፍ ዑመር ፋውንዴሽን (አሚባራ ግሩፕ) 32 ቤቶች መገንታቸውን እና ሁሉም ቤቶች ለነዋሪዎች መተላለፋቸውን ገልፀዋል።
ነዋሪዎች አዲስ ዓመትን በአዲስ ተስፋ እንዲጀምሩ ትልቅ አስተዋፅዖ ያበረከታችሁ ተቋማት እና የከተማችን ልበ ቀና ባለሃብቶችን በራሴ፣ በከተማ አስተዳደሩ እና በነዋሪዎቹ ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ ብለዋል ከንቲባዋ።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ 837 መኖሪያ ቤቶችን ለአቅመ ደካሞች እና ለሀገር ባለውለታ ነዋሪዎች አስተላለፉ

More Stories
ባለፉት ሦስት ዓመታት ለሰብዓዊ ድጋፍ በሚል የገባ ስንዴ የለም – አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም (ዶ/ር)
በገጠሩ የሀገሪቱ አካባቢዎች መንግስት የሚዘረጋቸውን የተለያዩ ኢንሸቲቦችን ቀድሞና ፈጥኖ ተግባራዊ ከማድረግ አንፃር የተሻሉ አፈጻጸሞች መታየታቸው ተገለፀ ።
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በ6 ጉዳዮች ላይ ውሳኔ አሳለፈ