የጃኮብ ዙማ ሴት ልጅ የኢስዋትኒ ንጉስ 16ኛዋ ሚስት በመሆን ተሞሸረችየጋብቻ ስነ ስርዓቱ ባሳለፍነው ሰኞ በኢስዋትኒ መዲና ሎባምባ ቤተ መንግስት ተካሂዷልአል-ዐይን 2024/9/5 15:22 GMTየቀድሞ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ጃኮብ ዙማ ብዙ ሚስቶች ያሏቸው ሲሆን 20 ልጆችንም አፍርተዋልየጃኮብ ዙማ ሴት ልጅ የኢስዋትኒ ንጉስ 16ኛዋ ሚስት በመሆን ተሞሸረች፡፡ኖምችዶ ዙማ የ21 ዓመት እድሜ ያላት የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ጃኮብ ዙማ ልጅም ናት፡፡የደቡብ አፍሪካ ጎረቤት የሆነችው የቀድሞዋ ስዋዚላንድ የአሁኗ ኢስዋትኒ ንጉሳዊ ስርዓት ያላት ሀገር ናት፡፡የፖለቲካ ፓርቲ ማቋቋም በህግ የከለከለችው ይህች ሀገር በንጉስ ምስዋቲ ሶስተኛ በመመራት ላይ ትገኛለች፡፡የ56 ዓመቱ የኢስዋትኒ ንጉስ የ21 ዓመቷን ኖምችዶ ዙማን 16ኛ ሚስት አድርገው ማግባታውን የሀገሪቱ ብዙሀን መገናኛዎች ዘግበዋል፡፡እንደ ዘገባዎቹ ከሆነ ጋብቻው 5 ሺህ ልጃገረዶች በተገኙበት ባህላዊ ስርዓቱን ጠብቆ ተካሂዷል፡፡
Al-Ain
More Stories
መንግስት በፈጠራና ክህሎት ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
ሀገራዊ የጤና ፖሊሲ ከመከላከልባሻገር አክሞ መዳንን መሰረት ያደረገ ስራን መስራት እንደሚገባ ተገለፀ።
በኢራን ወደብ በደረሰ ፍንዳታ 25 ሰዎች ህይወታቸው አለፈ