በዞኑ በ2017 የምርት ዘመን የቡና አቅርቦትና ጥራትን ለማሳደግ ብሎም ህገ ወጥ ንግድን ለመከላከል ከባለድርሻ አካለት ጋር የንቅናቄ መድረክ በቴፒ ከተማ አካሄዷል።በመድረኩ የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ እንደለጹት ዞኑ ዕምቅ የቡና ሀብት ያለዉ ቢሆንም በጥራት ማነስና በህገ ወጥ ንግድ መበራከት በየዓመቱ ለማዕከላዊ ገበያ የምቀርበዉ ምርት እየቀነሰ መምጣቱን ተናግረዋል።ለአብነትም በ2015 የምርት ዘመን 18 ሺህ የቀረበ መሆኑንና ይህም በ2016 ምርት ዘመን ወደ 14 ሺህ ቶን ዝቅ ማለቱን ዋና አስተዳዳሪዉ አንስተዋል። በ2017 የምርት ዘመን ጥራቱን የጠበቀ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ማቅረብ እንደሚገባ ያነሱት ዋና አስተዳዳሪዉ ቡና ለሀገራችን የዉጭ ምንዛሬ የሚያስገኝ በመሆኑ በጥራትና በህገ ወጥ ንግድ ቁጥጥር ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ያለድርድር በትኩረት እንዲሰሩ አሳስበዋል።የሸካ ዞን ግብርና ፣ አካባቢ ጥበቃና ህብረት ሥራ መምሪያ ኃላፊ አቶ አእምሮ ደሳልኝ ዞኑ ካለዉ የቡና ሽፋንና ምርት አንጻር ለማዕከላዊ ገበያ እየቀረበ ያለዉ ቡና በጥራት ማነስና በህገ ወጥ ንግድ ምክንያት በየዓመቱ እየቀነሰ በመምጣቱ ለዚህም የመፍትሔ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ከባለድርሻ አካላቱ እንዲረባረቡ ጠይቀዋል።ዘጋቢ ጌትነት ገረመዉ
በቡና ጥራትና ህገ ወጥ ንግድ ቁጥጥር ስርዓት ላይ በትኩረት እንዲሰራ የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ ጥሪ አቀረቡ ።

More Stories
ማህበረሰቡ በከባድ ዝናብ ምክንያት ከሚከሰቱ አደጋዎች እንዲጠነቀቅ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አሳሰበ።
የሰው ተኮር ተግባራት በማጠናከር ሁለተናዊ ዕድገትን ለማረጋገጥ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ ገለፁ።
የህዳሴው ግድብ መጠናቀቅ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ትስስርን ያሳድጋል