በ33ኛው ኦሊምፒክ ጨዋታዎች የ1 ሺህ 500 ሜትር የወንዶች ማጣሪያ ውድድር ኤርሚያስ ግርማ እና ሳሙኤል ተፈራ ወደ ግማሽ ፍጻሜ አልፈዋል፡፡በምድብ ሁለት የተወዳደረው ኤርሚያስ 3 ደቂቃ ከ35 ሴኮንድ ከ21 ማይክሮ ሴኮንድ በመግባት ነው ውድድሩን በቀዳሚነት በማጠናቀቅ ለግማሽ ፍፃሜ የበቃው፡፡በተመሳሳይ በምድብ ሶስት በዚሁ ርቀት የተወዳደረው ሌላኛው አትሌት ሳሙኤል ተፈራ 3 ደቂቃ ከ37 ሴኮንድ ከ34 ማይክሮ ሴኮንድ በመግባት ስድስተኛ ደረጃን በመያዝ ወደ ግማሽ ፍጻሜው የገባው።በምድብ አንድ የተወዳደረው አትሌት አብዲሳ ፈይሳ 14ኛ ደረጃን በመያዝ ማጣሪያውን ሳያልፍ ቀርቷል፡፡
በ1 ሺህ 500 የወንዶች ማጣሪያ ውድድር ኤርሚያስ ግርማና ሳሙኤል ተፈራ ወደ ግማሽ ፍጻሜ አለፉ

More Stories
ማንቼስተር ዩናይትድ ለአውሮፓ መድረክ…
ኢትዮጵያ ቡና ድሬዳዋ ከተማን አሸነፈ
የሊቨርፑልና ማንቼስተር ዩናይትድ የዋንጫ የበላይነት ፉክክር…