የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኢራን የኃይል መሠረተ ልማቶች ላይ ጥቃት ለመፈጸም ያስቀመጡትን የ48 ሰዓታት የጊዜ ገደብ ወደ አምስት ቀናት አራዘሙ።
ትራምፕ በመካከለኛው ምሥራቅ ስላለው ግጭት ከኢራን ጋር ሙሉ በሙሉ እና አጠቃላይ መፍትሔ መድረስን በተመለከተ ውይይቶች ማድረጋቸውን ገልጸዋል።
ፕሬዚዳንቱ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ÷ በኢራን የኃይል ማመንጫዎች እና የኢነርጂ መሠረተ ልማቶች ላይ የሚደረጉ ጥቃቶችን ለሌላ ጊዜ አስተላልፋለሁ ብለዋል።
ቴህራን የሆርሙዝ ወሽመጥን በ48 ሰዓታት ውስጥ ካልከፈተች የኃይል ማመንጫዎቿን ለማጥቃት የገለጹ ቢሆንም አሁን ግን ለመጪዎቹ አምስት ቀናት ርምጃቸውን እንዳዘገዩ አመላክተዋል።
ትራምፕ ከኢራን ጋር ባለፉት ሁለት ቀናት በመካከለኛው ምሥራቅ አለመረጋጋት ዙሪያ በጣም ጥሩና ውጤታማ ንግግር አድርገናል ማለታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
በዚህም የሀገራቸው ጦር በኢራን የኃይል መሠረተ ልማቶች ላይ ጥቃት እንዳይፈጽም ማዘዛቸውን ገልጸው÷ ጥቃቱን ለአምስት ቀናት እንደሚያዘገዩና ቀጣይ ውሳኔያቸው እየተካሄደ ባለው ንግግር ላይ እንደሚመሰረት አስታውቀዋል።
More Stories
የትራምፕ የ48 ሰዓት የጊዜ ገደብ እና የኢራን ምላሽ
ፕሬዚዳንት ትራምፕ ለኢራን የሰጡት የ48 ሰዓታት ገደብ ማስጠንቀቂያ…
እንግሊዝን ያስቆጣው የኢራን ጥቃት