ቻይና በመካከለኛው ምስራቅ እየተካሄደ ያለው ጦርነት እንዲቆም ኢራን፣ አሜሪካ እና እስራኤል ወደ ውይይትና ድርድር እንዲመጡ ጥሪ አቅርባለች፡፡
የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ሊን ጂያን በሰጡት መግለጫ÷ ኃይልን ብቸኛ አማራጭ ማድረግ የጦርነት አዙሪት ላይ መቆየት ብቻ እንጂ ሌላ ለውጥ አያመጣም ብለዋል፡፡
ጦርነቱ የሚቀጥል ከሆነ ወደ መካከለኛው ምስራቅ ቀጣና ሊስፋፋ ይችላል ያሉት ቃል አቀባዩ÷ ይህም ቀጣናውን ከቁጥጥር ውጭ ወደሆነ አስከፊ እልቂት ሊያስገባው እንደሚችል ማስጠንቀቃቸውን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡
ከቻይና ድርድር ጥሪ አስቀድመው ፕሬዚዳንት ትራምፕ ከኢራን ጋር ባለፉት ሁለት ቀናት በመካከለኛው ምስራቅ አለመረጋጋት ዙሪያ በጣም ጥሩና ውጤታማ ንግግር ማድረጋቸውን በማሕበራዊ ትስስር ገፃቸው ገልጸዋል፡፡
በዚህም በኢራን የኃይል መሠረተ ልማቶች ላይ ጥቃት ለመፈጸም ያስቀመጡት የ48 ሰዓታት የጊዜ ገደብ ወደ አምስት ቀናት ከፍ ማለቱ ተዘግቧል።
ትራምፕ ከኢራን ባለስልጣናት ጋር ጥሩና ውጤታማ ንግግር አደረኩ ይበሉ እንጂ በቴህራንና ዋሽንግተን መካከል ምንም አይነት ንግግር አለመደረጉን የሀገሪቱን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን ጠቅሶ ኢራን ኢንተርናሽናል ዘግቧል።
More Stories
ቦርዱ የፖለቲካ ፓርቲ ዕጩዎች በድምፅ መስጫ ወረቀት ላይ የሚኖራቸውን ቅደም ተከተል ለመወሠን የሚያስችለውን የዕጣ ማውጣት ሥነ-ሥርዓት በይፋ አስጀመረ
ትራምፕ በኢራን የኃይል መሠረተ ልማቶች ላይ ጥቃት ለመፈጸም ያስቀመጡትን የጊዜ ገደብ ወደ አምስት ቀናት አራዘሙ
የትራምፕ የ48 ሰዓት የጊዜ ገደብ እና የኢራን ምላሽ