March 21, 2026

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የ2026 የካራባኦ ዋንጫ ፍፃሜ …

ለአራት ዋንጫዎች እየተጫወተ እና ፕሪሚየር ሊግ እየመራ የሚገኘው አርሰናል ነገ ከተከታዩ ማንቸስተር ሲቲ ጋር የአመቱን የመጀመሪያ ዋንጫ ለማሳካት በካራባኦ ዋንጫ ፍፃሜ ይፋጠጣሉ።

አርሰናል ይህን ዋንጫ 2 ጊዜ(1987-1993) ብቻ ያነሳ ሲሆን ከ1993 ወዲህ 3 ጊዜ ለፍፃሜ የደረሰ ቢሆንም ሶስቱንም ተሸንፎ ዋንጫውን ሳያሳካ ለ33 አመት ዘልቋል።

ማንቸስተር ሲቲ በተቃራኒ የአርሰናልን 4 እጥፍ(8) የሚሆን የካራባኦ ዋንጫ አሸንፏል።

ማንቸስተር ሲቲ ዋንጫውን ለ4 ተከታታይ አመታት(2018-2019-2020-2021) በማንሳት ከሊቨርፑል ጋር ክብረወሰኑን መጋራት ችሏል።