March 21, 2026

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

እንግሊዝን ያስቆጣው የኢራን ጥቃት


ኢራን ፤በዩናይትድ ኪንግደም እና በአሜሪካ ጦር ይዞታዎች ላይ የሚሳዔል ጥቃት ማድረሷ ለንደንን አስቆጣ፡፡

በህንድ ውቅያኖስ ቻጎስ ደሴቶች ዴጎ ጋረሲያ ላይ ኢራን 3 ሺህ 800 ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ ጥቃት ማድረሷ ለእንግሊዝ ስጋት ጋርጦባታል ፡፡

ሁለት መካከለኛ ርቀት ተዋንጫፊ ባሊስተክ ሚሳኤሎች ቢተኮሱም በጦር ሰፈሩ ላይ ጉዳት ሳያደርሱ መክሸፋቸውም ተነግሯል፡፡

ኢራን ከ2 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ የሚምዘገዘግ ሚሳዔል የለኝም በሚል ሀሳብ መሰጠቷ ቢታወስም አሁን ላይ ግን እጥፍ መጓዝ የሚችልን ሚሳዔል ማሳየቷ አውሮፓውያንም እያስኮረፈ ይገኛል ፡፡

ዩናይትድ ኪንግድም በዚህ ጦርነት ላይ እጇ ሳይኖር ለምን ተጠቃች የሚል ጥያቄም መነሳት ተጀምሯል ፡፡

ቴህራን በራሷ ጊዜ ጠላት እያበዛች መሆኑን የዶሃ ኢንስቲትዩቱ ተንታኝና መምህር ሙሃናድ ሰሉም ጠቁመዋል ፡፡

የዩኬ-ዩኤስን የጦር ሰፈር በህንድ ወቅያኖስ መምታት ይህኑ የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል ፡፡
የጦርነቱን ሒሳባዊ ስሌት የሚለውጥ ነው፤ምዕራባውያን ከኢራን በተቃራኒው እንዲቆሙ ያስገድዳቸዋል ብለዋል ባለሙያው፡፡

ኢራን ከዚህ ቀደም ታይቶ የማይታወቀውን ሚሳዔል ማለትም እስከ 4 ሺህ ኪሎ ሜትሮች የሚመዘገዘግ መሆኑን ማረጋገጧ ነገ በእኔ ላይ ነወ የሚል ትምህርት አንዲወስዱ እንግሊዚችን ያስገድዳቸዋል ተብሏል ፡፡

ኢራን ለንደን የሚደርስ አህጉር አቋርጦ አውዳሚ ሚሳዔል (አይ ሲ ቢ ኤም ) ሊኖራት እንደሚችል ያሳያል ሚል መረጃም ተጋርቷል ፡፡

የአሜሪካ ምድር መዘልቅ የሚችል የጦር መሳሪያ ባለቤት ልትሆን እንደምትችልም ግምቶች እንዲቀመጡ እያደረገ ነው ብለዋል የዶሃው መምህርና ተንታኝ ፡፡

ለዚህም ነው ዩናይትድ ኪንግደም ኢራን በብሄራዊ ጥቅሞቻችን ላይ እየመጣች ነው በሚል ያወገዘችው፡፡

እንዲህ ዓይነቱ አካሄድ ደግሞ ዩናይትድ ኪንግደምን ጨምሮ በርካታ የአውሮፓ አገራት በጦርነቱ ውስጥ አንሳተፍም ያሉትን አስገድዶ እንደማስገባት ሊወሰድ የሚችል ነው እየተባለ ይገኛል ፡፡

ዘገባው የዘልጀዚራ ነው ፡፡