March 20, 2026

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የሸካ ማህበረሰብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የእውቅና ሴርቲፍኬት ተሰጠው

ማሻ፤ መጋቢት 9/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) የሸካ ዞን ምክር ቤት ባካሄደው  5ኛ ዙር 13ኛ ዓመት የስራ ዘመን 24ኛ መደበኛ ጉባኤው የሸካ ማህበረሰብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በተቋቋመ አጭር ጊዜ ውስጥ ላስመዘገው አመርቂ ውጤት የምስክር ወረቀት ተሰጥቶታል።

ተቋሙ የዞኑን ሕዝቦች የሚዲያ ተጠቃሚነት ወደተሻለ ደረጃ ለማድረስና የመረጃ ተደራሽነትን ለማስፋት ውጥን ይዞ እየሠራ የሚገኝ ስለመሆኑና ባጭር ጊዜ ውስጥ ያከናወናቸው ተግባራት የሚደነቁ መሆናቸው ተገልጿል።

ከዚህ ቀደም በነበሩት ጊዜያት ሚዲያ ባለመኖሩ የዞኑን ሕዝብ ባህላዊና ማህበራዊ  እሴቶች ለማጉላት እንዲሁም ተፈጥሯዊና ታሪካዊ ሀብቶቹን ለማስተዋወቅ ውስንነቶች መኖራቸውን የጠቆሙት የዞኑ ተወላጅና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ አልማው ዘውዴ የዞኑን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞን ጨምሮ የተቋሙ ሠራተኞች፣ የቦርድ አመራሮችና አባላት ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል።

የዞኑ ሕዝቦችና ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ተቋሙ ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆን ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጠይቀዋል።

የዞኑ ምክር ቤት ከምስረታው አንስቶ ድጋፋዊ ክትትሎችን ማድረግን ጨምሮ በሌሎችም ጉዳዮች ፈጣን ምላሽ እየሰጠ ከመሆኑም ባሻገር በ5ኛ ዙር 13ኛ ዓመት የስራ ዘመን 24ኛ መደበኛ ጉባኤው በአቶ አልማውና በክልሉ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሀላፊ አቶ የሺዋስ ዓለሙ በኩል ለተቋሙ የእውቅናና የማበረታቻ የምስክር ወረቀት በመስጠት ዘላቂ አጋርነቱን አሳይቷል።