March 17, 2026

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ከ90 በላይ ኩባንያዎች የሚሳተፉበት ዓለም አቀፍ አውደርዕይ ሊካሄድ ነው

ማሻ፤ መጋቢት 8/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) 10ኛው ኢትዮ ኸልዝ ዓለም አቀፍ አውደርዕይና ጉባኤ እንዲሁም 2ኛው የሀገር ውስጥ የህክምና ግብዓት ምርትና ኢኖቬሽን ኤግዚቢሽን በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ሴንተር እንደሚካሄድ ተገልጿል።

አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን እና አቅራቢዎችን ለሀገራችን በማስተዋወቅ፣ የቴክኖሎጂ እና የዕውቀት ሽግግርን በማምጣት ለዘርፉ ልማት በሚደረገው ጥረት ውስጥ ቁልፍ መድረክ እንደሆነ ተጠቁሟል።

በዘርፉ ተዋናዮች መካከል የንግድ ልውውጥን በማሳደግ እና የገበያ ትስስርን የመፍጠር ዕድል እንዳለውም ተነስቷል።

የዘንድሮው ኹነት ከሥምንት አገራት የተውጣጡ ከ90 በላይ ኩባንያዎች የሚሳተፉበት እንደሆነ ነው የተነገረው።

በተጨማሪም ከ40 በላይ የሙያ ማጎልበቻ (CPD) ስልጠናዎች፣ 3ኛው የዲጂታል ኸልዝ እና ሳይንሳዊ ፎረሞች የኹነቱ አካል ናቸው ተብሏል።

2ኛው የሀገር ውስጥ የህክምና ግብዓት ምርትና ኢኖቬሽን ኤግዚቢሽን የሚካሄድ ሲሆን የሀገር ውስጥ የህክምና መሣሪያዎች፣ የመድኃኒት አምራቾች እና የጤና ቴክኖሎጂ ፈጠራዎችን ለማበረታታትና ለገበያ ለማቅረብ የሚረዳ መሆኑ ተገልጿል።

(አራዳ ኤፍ ኤም)