March 9, 2026

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የኮንታ ዞን የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የአመራር ግምገማና ምዘና መድረክ በአመያ ከተማ መካሄድ ጀምሯል።

ማሻ፤ የካቲት 30/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የባህል፤ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ፋንታሁን ብላቴ በምዘና መድረኩ እንደገለጹት ባለፉት 6 ወራት በዞኑ በፓርቲና መንግስት የተከናወኑ ተግባራትን በመፈተሽ አመራሩን ለቀጣይ ተልዕኮ ዝግጁ የማድረግ ዓላማ ያነገበ ግምገማ መሆኑን ገልጸዋል።

ሁለንተናዊ ብልጽግና የማረጋገጥ ራዕይን እውን ለማድረግ የአመለካከት ጥራት፣ የአመራር ሰጭነት ብቃት፣ የታነፀ ስነ ምግባር የተላበሰ፣ በእውቀት እና በአፈፃፀም የበቁ እና የላቁ አመራርን ለመፍጠር ዓላማ ያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

በመደመር መንግስት እሳቤ ተልዕኮን በመፍጠር፣ በመፍጠን እንዲሁም በዝላይ በመተግበር የተከናወኑት ተግባራት በጥልቀት የሚገመገም መሆኑንም ጠቁመዋል።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ህግና ፍትህና መልካም አስ/ር ጉዳዮች አማካሪ አቶ ዳግም ዳንኤል እንደገለጹት በአመራሩ ዉስጥ በተግባራት አፈፃፀም የሚታዩ ጉድለቶች ፈትሾ የማጥራት ስራ የሚሰራበት መሆኑን ገልጸው በጥንካሬ የታዩትን ይበልጥ ለማጎልበት፣ ጉድለቶችን ለማረምና በአመራሩ መካከል የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት አጠናክሮ ማስቀጠልን ያለመ መድረክ መሆኑን አንሰተዋል።

አመራሩ ባለፉት ጊዜ ከተገመገሙ ነጥቦች ለመውጣት ያደረገው ህደት በዝርዝር ተነስቶ እንደምገመገም አንስቷል። በተለይ የፓርቲያችን ኢንሼቲቮችን ውጤታማ በማድረግ የሕዝቡን ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ አኳያ ተግባሩ የተመራበት አግባብ መገምገም እንዳለበት ተነስቷል።

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታከለ ተስፉ መድረኩ በፓርቲ መሪነት የተሰሩ ስራዎችን በመገምገምና በመፈተሽ ጠንካራ አመራር መገንባትን ዓላማ ያደረገ መሆኑን አንስተዋል።

አንድ ጠንካራ የአመራር ስርዓት ለበለጠ ውጤታማነት የጎላ ሚና ያለው በመሆኑ ይህን የግምገማ መድረክ እንደ መልካም አጋጣሚ መጠቀም እንዳለብን አንስተዋል ።

መድረኩ እርስ በእርስ መገነባባት የሚያስችልና ወጥ የሆነ አሰራር እንዲሰፍን ከማስቻሉ በተጨማሪ የብልጽግና ፓርቲ ያስቀመጣቸውን ራዕይ እና ተልዕኮ በጥብቅ ዲሲፕሊን እንዲመሩ ፋይዳው የጎላ እንደሆነ ገልጸዋል ሲል የዞኑ መንግስት ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።