ማሻ፤ የካቲት 30/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) የኢራን የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊ አሊ ላሪጃኒ፤ አያቶላ ሙጅተባ ካሜኒ አባታቸውን ተክተው መመረጣቸው እስራኤልን እና አሜሪካን “ለተስፋ መቁረጥ” ዳርጓቸዋል ብለዋል።
ላሪጃኒ ዛሬ በኤክስ (X) ማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት “በኢራን የሃይማኖት ሊቃውንት ጉባኤ የኢስላማዊት ሪፐብሊክ መሪ ሆነው መመረጥዎ ጠላት እና ጦርነት ፈላጊ የሆኑ ባላንጣዎቻችን ተስፋ እንዲቆርጡ አድርጓል” ሲሉ ገልጸዋል።
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንም አባታቸው በአሜሪካ እና በእስራኤል ጥቃት መገደላቸውን ተከትሎ የተሾሙትን አዲሱን የኢራን የበላይ መሪ ሞጅታባ ካሜኒን “የማይናወጥ ድጋፍ” እንደሚያደርጉላቸው ቃል ገብተዋል።
ፑቲን አክለውም “ኢራን የትጥቅ ጥቃት እየተጋፈጠች ባለችበት በዚህ ወቅት፣ በዚህ ከፍተኛ የሥልጣን እርከን ላይ የምታደርጉት ቆይታ ታላቅ ድፍረትና ቁርጠኝነትን እንደሚጠይቅ ጥርጥር የለውም” ብለዋል።
በተመሳሳይ ቻይና የአዲሱን የኢራን መሪ ኢላማ የማድረግ ሙከራን እንደምትቃወም አስታውቃለች። ቻይና ይህን ያለችው የእስራኤል ጦር አሊ ካሜኒን የሚተካ ማንኛውንም መሪ ኢላማ እንደሚያደርግ መዛቱን ተከትሎ ነው።
የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጉኦ ጂያኩን ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የካሜኒ ሹመት የሀገሪቱ የውስጥ ጉዳይ ብቻ መሆኑን ገልጸዋል።
More Stories
“ሞጅታባ እንኳን ደስ አለህ “ፑቲን
አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እና ድሮኖች አረምን ለመከላከል እየረዱ ነው፡፡
ዓለም አቀፉ የነዳጅ ዋጋ ጨመረ