ማሻ፤ የካቲት 30/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) ዓለም አቀፉ የነዳጅ ዋጋ ከፍተኛ ጭማሪ ማሳየቱ ተሰምቷል።
በመካከለኛው ምስራቅ በተፈጠረው ቀውስ ሳቢያ አሁን ላይ አንድ በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ከ110 ዶላር በላይ በሆነ ዋጋ እየተሸጠ ይገኛል።
ይህም ከፈረንጆቹ 2022 ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ተብሏል።
የንግድ መርከቦች መተላለፊያ የሆነው የሆርሙዝ ወሽመጥም የተዘጋ ሲሆን፥ አሜሪካ እና እስራዔልም የኢራንን የነዳጅ ማከማቻዎች በሚሳኤል ማውደማቸው ታውቋል።
ይህን ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ ከፍተኛ ጭማሪ ያሳየ ሲሆን፥ በእስያም ከ114 ዶላር በሆነ ዋጋ እየተሸጠ መሆኑን ቢቢሲ በቢዝነስ ዘገባው አመላክቷል።
ከዚህ ባለፈም በተለያዩ አካባቢዎች የአክሲዮን ገበያ ከፍተኛ ቅናሽ ማሳየቱንም ዘገባው አመላክቷል።
ከዚህ ጋር በተያያዘም ቻይና የተፈጠረው ቀውስ የሚፈታበትን መንገድ ለማመቻቸት ልዑኳን ወደ ሳዑዲ የላከች ሲሆን፥ የቡድን ሰባት አባል አገራት ሚኒስትሮች ደግሞ በነዳጅ ዋጋ ላይ ለመምከር ዛሬ ይሰበሰባሉ።
#(አራዳ ኤፍ ኤም)
More Stories
“ሞጅታባ እንኳን ደስ አለህ “ፑቲን
የኢራን ጦርነት ዐበይት መረጃዎች፡ አያቶላህ አሊ ኻሜኒ መገደላተውን ተከትሎ ሞጅታባ ካሜኒ በአባታቸው ምትክ ተመረጡ
አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እና ድሮኖች አረምን ለመከላከል እየረዱ ነው፡፡