ማሻ፤ የካቲት 27/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) ለሁለት ቀናት ስካሄድ የቆየው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የአጠቃላይ አመራር ግምገማና ምዘና መድረክ ተጠናቋል።
በመድረኩ የማጠቃለያ ሀሳብ የሰጡት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድሩ ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)፥ አመራሩ የተግባር ውጤታማነት በማሳደግ የህዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ መትጋት አለበት ብለዋል።
ምዘናው ተልዕኮን በብቃት የሚወጣ አመራር በመፈጠር፣ ተቋማት የተጣለባቸውን የህዝብና የመንግሥት ኃላፊነት በተሻለ መልኩ እንዲፈጽሙ የሚያስችል ነው ብለዋል ርዕሰ መስተዳድሩ።
አመራሩ ለፓርቲው ያለውን ውግንና በግልፅ ማሳየት፣ አሉታዊ አስተሳሰቦች መሟገትና ማረም እንደሚገባ ያስገነዘቡት ርዕሰ መስተዳድሩ፥ በሂደቱ የሚስተዋሉ ብልሽቶችን በመለየት ተጠያቂነት የማስፈን አሰራር ይዘረጋል ብለዋል።
አመራሩ የፓርቲ ተልዕኮ አልቆ መወጣት እንዳለበት ያስገነዘቡት ዶ/ር ነጋሽ፥ በብልፅግና ፓርቲ መርህ ላይ ቆሞ የአመለካከትና የአስተሳሰብ ጥራት ማረም ይገባል ብለዋል።
አመራሩ የተጣለበትን የመንግሥት የህዝብ ኃላፊነት ለመወጣት ከመቼውም ጊዜ በበለጠ በጊዜ የለኝም ስሜት ራሱ ለተግባር ውጤታማነት ማዘጋጀት እንዳለበትም ነው ርዕሰ መስተዳደሩ ያስገነዘቡት።
ምዘናው የአመራር የአመለካከትና የተግባር ውጤታማነት በዝርዝር መገምገሙን የገለጹት የክልሉ የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ፍቅሬ አማን፥ አመራሩ ራሱ መልሶ እንዲመለከት በማድረግ ለቀጣይ ተልዕኮ ያዘጋጀ ነው ብለዋል።
አመራሩ የብልፅግና ፓርቲ መሠረታዊ ዕሴቶችን በመከተል አብሮነትና አንድነት እንዲሁም ውንድማማችነትና እህትማማችነት በማኅበረሰብ ውስጥ ማጠናከር እንደሚገባም አቶ ፍቅሬ አሳስበዋል።
ማኅበረሰብን ለማገልገል በፍጹም ልብ በመስጠት ተግባራት በተሻለ ውጤታማነት መፈጸም ይገባል ያሉት አቶ ፍቅሬ፥ በምዘናው በጉድልት የተገመገሙ ችግሮችን ፈጥኖ ማረም እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
አመራሩ በአንድ አሃድ በመኾን የውስጥና የውጪ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በልዩ ትኩረት መፍታት እንደሚገባ የጠቆሙት አቶ ፍቅሬ፣ የአገልግሎት አሰጣጥ በማሻሻል ችግሩን በዘላቂነት መፍታት ይገባል ብለዋል።
More Stories
ህንድ ከሩሲያ ነዳጅ እንዳትገዛ የተጣለው ማዕቀብ ለ1 ወር ተነሳላት
በመካከለኛው ምሥራቅ የተባባሰው ጦርነት ከተለኮሶ ዛሬ ስድስተኛ ቀኑን ያዘ።
ታሪካዊ ስህተትን የማረም ጉዞ …