March 4, 2026

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ሸካ ዞን የማሻ ከተማ ምክር ቤት 2ኛ ዙር 13ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤ በማሻ ከተማ ተካሄደ።

በ6ወር አፈፃፀም ከቀረቡት ሪፖርቶች መካከል በትምህርት ዘርፍ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት መጠናከር እንዳለባቸው የማሻ ከተማ የምክር ቤት አባላት ገለፁ።

ምክር ቤቱ ባካሄደው 2ኛ ዙር 13ኛ አመት የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤ በ2018 በጀት አመት የመጀመሪያ አፈጻጸም ሪፖርት በማሻ ከተማ ከንቲባ በአቶ አንዷለም ጌታቸዉ ቀርበዋል።

በትምህርት ዘርፍ የት/ቤቶች የዉስጥ ገቢ ከማሳደግ አኳያና የተማርዎች ምገባ ዙሪያ ሰፊ ዉይይት ተደርጎ የንቅናቄ መድረክ በማካሄድ ወደ ትግበራ የተገባ ሲሆን ፤በንቅናቄዉም በከተማና በቀበሌ ደረጃ 331በየደረጃዉ የሚገኙ የህ/ሰብ ክፍሎችን ለማሳተፍ ተችሏል ብሏል።

አቶ አንዷለም አክለው ትምህርት ቤቶችን ዉብና ምቹ የማድረግ ስራ በሁሉም ት/ቤቶች የተሰራ መሆኑን፣አብዛኛዎቹን ለእርሻ የማሆኑ ቦታዎችን በማልማት በበቆሎ፣በአተር፣በባቄላና ለሎች አትክልቶች የመሸፈን ሥራ መሠራቱን ተናግረዋል።

የልዩ ድጋፍ ትምህርትን በተመለከተ ተማሪዎች በክልል አቀፍና አገር አቀፍ ፈተና የተሻለ ዉጤት እንድያስመዘግቡ በ6ኛ ፤8ኛ ክፍል እና በ12ኛ ክፍል ላይ ልዩ የማጠናከርያ ትምህርት በሁሉም ትምህርት ቤቶች እየተሰጠ ይገኛል ብለዋል።

የምክር ቤቱ አባላት በበኩላቸዉ ሪፖርቱ ግልፅ እንደሆነ አዉስተዉ የመንግስት ትኩረት የምሹ ጉዳዮች መካከል እንዱ የትምህርት ስብራትን ለመጠገን በትኩረት መሰራቱን ገልፀው ጉድለቶችን በማረም ቀጣይ ውጤታማ ለውጥ ማስመዝገብ እንደሚገባ ጠቁመዋል ።

የማሻ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፋ አቶ ማንደፍሮ እንደሻዉ በበኩላቸዉ በምክር ቤት አባላት የተነሳዉ ሀሳብ ገንብ እንደሆነ ገልፀዉ የመፀሐፍ እጥረትን ለመቅረፍ መንግስትም የራሱ ድርሻ እንዳለ ሆኖ ህብረተሰቡም ሊያግዝ ይገባል ሲሉ ጠይቀዋል።