March 3, 2026

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

7ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ ”ማኒፌስቶ” እና የምርጫ ምልክት ማስተዋወቂያ መርሃግብር በሸካ ዞን የማሻ ወረዳ የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት አካሄደ።

ማሻ፤ የካቲት 24/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) “ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!” በሚል መሪ ቃል፣ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ምልክትና ማኒፌስቶ ማስተዋወቂያ  መድረክ በማሻ ከተማ በድምቀት ተካሂዷል።

በመርሃ ግብሩ ንግግር ያደረጉት የወረዳው የመንግስት ተጠሪ አቶ ደመቀ ወልደዬስ  ኢትዮጵያ ወርቃማው ጊዜ ላይ እንደምትገኝ ገልፀው እንዲሁም እምቅ ሀብቶቿን ማልማት የጀመረችበትና ጂኦ ፓለቲካዊ ቁመናዋም  እየተቀየረ መምጣቱንም ተናግረዋል።

ሀገር በምክክር ችግሮቿን እየሻረች፣ነገዋን እየተለመች በመሆኑ ኢትዮጵያ በብዙ መንገዶች ራሷን የመቻል ዕቅዷን እያሳካች እንደምትገኝም ገልፀዋል።

በዚህም የኢትዮጵያን ህልም እውን ሆኖ ሁለንተናዊ ብልጽግና በኢትዮጵያ እንዲረጋገጥ ጉዞውን በውጤት መጀመሩንም ተናግረዋል።

ይሄን ውጤታማ ጉዞ ይበልጥ ለማሳካት ብልፅግናን መምረጥ ወሳኝ ጉዳይ መሆኑንም አክለዋል።

በዚህም የኢትዮጵያን ህልሞች ለማሳካት  በ2023 ኢትዮጵያን የአፍርካ ተምሳለት መድረግ፣ በ2040 ከሁለት ታላላቅ የአፍርካ ኢኮኖሚዎች አንዷ ማድረግና ከሀያ የኢኮኖሚ ሀገራት ተርታ ማሰለፍ የሚሉት ማሳካት መሆንም ጠቁመዋል።

የማሻ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መስፍን አዳሾ  በበኩላቸው  የኢትዮጵያ ጂኦ ፓለቲካዊ ትልሟን ለማሳካት እየተሰራ በመሆኑ በህዝቡ ተጠቃሚነት ላይ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

ኢትዮጵያ ማደግ በሚገባት ልክ ያለመበልፀጉዋን ተናግረው ዕድገቷ እንዲፋጠን ለማድረግ ክልሉ በመመስረቱ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በማስጀመር ላይ እድገት እያሳየ ነው ብለዋል።

ሰላምን ለልማት ልማትን ለሰላም በማድረግ በዞኑ የነበሩ ያለመግባባቶችን በመቅረፍ ከዕዳ ወዴ ምንዳ በመሻገር በወረዳው ያሉ ለሚ መሬቶችን በመጠቀም የተሻለ ውጠት ተመዝግቧል ነው ያሉት።

በሌላ በኩል ቀጣይነት ያለው የማዳበሪያ ፋብሪካ ፣የነዳጅ ማጣሪያ ግንባታና ግዙፍ የአየር ጥሮጀክቶችን ለማሳት እየተሰራ ሲሆን አምራችና ሸማቹን በማገናኘት ህብረተሰቡ ተጠቃሚ እንዲሆን እየተሰራ ይገኛል።

እነዚህና ሌሎችን ለማሳካት ብልፅግናን ይምረጡ ሲሉ ዋና አስተዳዳሪው ገልፀው ምልክቱም የስንዴ ነዶ ሲሆን ምልክቱ የመደመር፣ የአንድነት እና የሉዓላዊነት መገለጫ መሆኑንም ጠቁመዋል።