February 23, 2026

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የሸካቾ ብሔረሰብ ባህላዊ አስተዳደር  ምክክር

ማሻ፤ የካቲት 16/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) የሸካቾ ብሔረሰብ ባህላዊ አስተዳደር ንጉስ ቴቺ ቀጆቺና ምክረቾ አባላት ከማሻ ከተማና ወረዳ መዋቅር ከተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በማሻ ከተማ ግሪንላላድ ሆቴሉ እየመከሩ ነው።
👉 የባህላዊ አስተዳደር መዋቅሩ ተግባራዊ ከተደረገ ወዲህ የሰሩ ስራዎችን የተመለከ ሪፖርት
👉 በባህላዊ አስተዳደርና ህዝብ የጸደቀው ቲሞና ሼሮ አፈጻጸም እና አተገባበር
👉 ስር የሰደዱና ለማህበራዊ መስተጋብር መናድ አበርክቶ ያላቸውን ወንጀል ነክ ተግባራትን ከስሩ ለማስቀረት
👉  ንጉሱ በሚመሩት በዚህ መድረክ መቋጫ ያላገኙ ጉዳዮች አቅጣጫ ይመላከትባቸዋል ተብሎ ይጠበቃል።
👉 ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በማሻ ከተማ የተከሰተውን የረቀቀ ወንጀልና ስርቆት በተመለከተ ህዝቡ ለቀናት በአውጣጭኝ የሰጣቸው መረጃዎችን በተመለከተም ወይይት ተደርጎ መደሚደሚያ እንደሚያገኝ ይጠበቃል።
በውይይቱ የሀይማኖት አባቶች፣ የጎሳ መሪዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ከተለያዩ ማህበራዊ መሰረቶች ህዝብ የወከሉ የወረዳና ከተማ ነዋሪዎች እየተሳተፉ ነው