የማላዊ፣ የብሩንዲ፣ የናይጄሪያ፣ የዛምቢያ እና የኮንጎ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በ39ኛው የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ዛሬ ምሽት አዲስ አበባ ገብተዋል።
ሚኒስትሮቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዴኤታ አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ የካቲት 7 እና 8 ቀን 2018 ዓ.ም የሚካሄድ ሲሆን፤ ከጉባኤው አስቀድሞ የካቲት 4 እና 5 ቀን የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት 48ኛው መደበኛ ስብሰባ ይካሄዳል።
ጉባኤው “የአጀንዳ 2063 ግቦችን ለማሳካት ዘላቂ የውኃ አቅርቦትና አስተማማኝ የንጽህና አጠባበቅ ሥርዓቶችን ማረጋገጥ” በሚል መሪ ቃል ነው የሚካሄደው።
More Stories
የአፈር ማዳበሪያ ተጠቃሚ መሆን…
በዓለም ላይ ከፍተኛ ቀውስ እያስከተለ በሚገኘው ጦርነት እስካሁን ምን ተከሰተ?
ኢራን “እራሴን ለመከላከል የምፈጽመውን ጥቃት አጠናክሬ እቀጥላለሁ” አለች