February 4, 2026

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የማሻ ቅርንጫፍ ለአርሶአደሮች የግብርና ብድር እንደሚሰጥ አስታወቀ

ማሻ፤ ጥር 19/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) የሸካ ዞን ማሻ ወረዳ ግብርና ፅህፈት ቤትና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ማሻ ቅርንጫፍ መካከል በወረዳው በግልም ሆነ በቡድን ለተደራጁ አርሶአደሮች የግብርናን ዘርፍ ምርታማነት ለማሳደግ የታለመ የብድር ስምምነት መደሰሱ ተገልጿል።

እንደሀገር መንግስት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ለአርሶአደሮች ለግብርና ስራ የሚሆኑ ግብዓቶችን ለሟሟላት ነውም ተብሏል።

የማሻ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መስፍን አዳሾ መንግስት የአርሶአደሩን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሰራ መሆኑን በመግለፅ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኩል ብድር መዘጋጀቱን ተናግረዋል።

አያይዘውም የወረዳ አርሶአደሮች የተዘጋጀው የብድር አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ የግንዛቤ ስራ መስራት እንደሚያስፈልግ ገልፀው ለባንኩ ቅርንጫፍ ምስጋና አቀርበዋል።

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የማሻ ቅርንጫፍ ስራአስኪያጅ አቶ ገመቺስ አስራት በበኩላቸው የብድር ሁኔታን በተመለከተ ገለፃ ያደረጉ ሲሆን ለተነሱ ጥያቄዎችም ማብራሪያ ሰጥተዋል።

መንግስት እያመጣ ያለውን ምቹ አጋጣሚ በመጠቀም ባንኩ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት አርሶአደሮች ተበድረው እንዲጠቀሙ አቶ ገመቺስ ጠይቀዋል።

የቀረበው ሰነድ ላይ የወረዳ አስተዳደር ፣የወረዳ ግብርና ንፅህፈት ቤትና የቀበሌ አስተዳዳሪዎች መካከል ስምምነት ተደርጓል።