February 4, 2026

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

አርሰናል ኢንተር ሚላንን አሸነፈ

ማሻ፤ ጥር 12/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የ7ኛ ዙር መርሐ ግብር ዛሬ ምሽት ዘጠኝ ጨዋታዎች ተደርገዋል።

በሻምፒየንስ ሊጉ በዚህ የውድድር ዓመት በብቸኝነት ሁሉንም ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው አርሰናል ወደ ጣሊያን አቅንቶ ምሽት 5 ሰዓት ኢንተር ሚላንን ገጥሟል።

በዚህም ኢንተር ሚላንን 3 ለ 1 በመርታት በሻምፒየንስ ሊጉ የአሸናፊነት ጉዞውን አስቀጥሏል።

በሌሎች የሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታዎች ሪያል ማድሪድ ሞናኮን 6 ለ 1 ፣ ስፖርቲንግ ሊዝበን ፒኤስጂን 2 ለ 1፣ ቶተንሃም ሆትስፐር ቦሩሺያ ዶርትመንድን 2 ለ 0፣ አያክስ አምስተርዳም ከሜዳው ውጪ ቪያሪያልን 2 ለ 1 እንዲሁም ኦሎምፒያኮስ ባየር ሊቨርኩሰንን 2 ለ 0 አሸንፈዋል።

ኮፐንሀገን እና ናፖሊ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል።

ቀደም ሲል ምሽት 2 ሰዓት ከ45 በተደረገ ጨዋታ ወደ ኖርዌይ ያቀናው ማንቼስተር ሲቲ በቦዶ ግሊምት 3 ለ 1 የተሸነፈ ሲሆን፤ ቀደም ብሎ ምሽት 12 ሰዓት ከ30 በተደረገው የዕለቱ የመጀመሪያ መርሐ ግብር ክለብ ብሩጅ ካይራት አልማቲን 4 ለ 1 ማሸነፉ ይታወቃል፡፡