ማሻ፤ ጥር 09/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) በ22ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር አርሰናል እና ኖቲንግሃም ፎረስት 0 ለ 0 ተለያይተዋል።
ምሽት 2፡30 ላይ የተካሄደው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ያለምንም ግብ የተጠናቀቀ ሲሆን÷ አርሰናል በሊጉ በሁለተኛ ደረጃ ከሚከተለው ማንቼስተር ሲቲ ያለውን ልዩነት ወደ 9 ማስፋት የሚችልበትን ዕድል ሳይጠቀምበት ቀርቷል።
ቀደም ብለው በተደረጉ ጨዋታዎች ማንቼስተር ዩናይትድ ማንቼስተር ሲቲን እንዲሁም ቼልሲ ብሬንትፎርድን 2 ለ 0 ሲያሸንፉ ሊቨርፑል እና በርንሌይ 1 ለ 1 አቻ ተለያይተዋል።
በተጨማሪም ሰንደርላንድ ክሪስታል ፓላስን 2 ለ 1፣ ሊድስ ዩናይትድ ፉልሃምን 1 ለ 0 ሲያሸንፉ÷ ዌስትሀም ዩናይትድ ቶተንሃምን 2 ለ 1 መርታት ችለዋል።
More Stories
የ2026 የካራባኦ ዋንጫ ፍፃሜ …
ሴኔጋል የአፍሪካ ዋንጫ ሻምፒዮንነቷ እንዲሰረዝ መወሰኑ አሳፋሪ ነው፡- የካፍ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ኦጉስቲን ሴንግሆር
ቦርንማውዝ ከ ማንችስተር ዩናይትድ