ማሻ፤ ጥር 09/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) ብፁዕነታቸው ከከተራ እስከ ቃና ዘገሊላ ያለውን የጥምቀት በዓል ባማረና በደመቀ እንዲሁም ሀይማኖታዊ ትውፊቱን በጠበቀ መልኩ ለማክበር በሁሉም አካባቢዎች ዝግጅት መደረጉን ነው ያመላከቱት።
ጥምቀት ከጨለማ ወደብርሃን የተሻገርንበት፣እዳችን የተሰረዘበት፣ከወደቅንበት የተነሳንበትና የተጣላ የሚታረቅበት የድነት በዓል በመሆኑ በጉጉት የሚጠበቅ በዓል መሆኑንም አንስተዋል።
በዩኔስኮ ከማይዳሰሱ የአለም ቅርሶች አንዱ የሆነው ጥምቀት አብሮነትን የሚያጠናክር በመሆኑ ኢትዮጵያውያንን በአጠቃለይ የሚወክል ነው ብለዋል።
ታቦታቱ ከመንበራቸው ወጥተው ወደ ጥምቀተ ባህር የሚሄዱበት ሂደት ኢየሱስ ክርስቶስ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ ለመጠመቅ የሄደበትን ማሳያ እንደሆነ ገልፀዋል።
በዓሉን የተቸገሩ ወገኖችን በመደገፍ ልናሳልፍ ይገባልም ነው ያሉት።
ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በአሉ የፍቅርና የአብሮነት እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል።
#Southwestmedianetwork
More Stories
እንግሊዝን ያስቆጣው የኢራን ጥቃት
በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ በሌማት ትሩፋት መርሐግብር የተሠማሩ ወጣቶች ተጠቃሚ እየሆኑ መምጣቸው ተገለጸ።
ኢራን ላይ እየተካሄደ የሚገኘው ወታደራዊ ዘመቻ …