ማሻ፤ ጥር 09/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ባለፉት ስድስት ወራት ከ8 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ተሰብስቧል አለ የክልሉ ገቢዎች ቢሮ፡፡
የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ህይወት አሰግድ እንዳሉት፥ በክልሉ የሚሰበሰበውን ገቡ ለማሳደግ ለግብር ከፋዩ ማህበረሰብ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮችን በማዘጋጀት በተከታታይነት ሲሰራ ቆይቷል፡፡
እነዚህ ስራዎች ለገቢው ማደግ አስተዋፅኦ ማድረጋቸውን ገልጸው፥ ክልሉ ካለው ገቢን የማመንጨት አቅም አንፃር አሁንም በትኩረት እየተሠራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
በክልሉ ከተገኘው ገቢ ውስጥ ከ7 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ የሚሆነው ከመደበኛ ገቢ እንዲሁም ከ656 ሚሊየን ብር በላይ ከማዘጋጃ ቤታዊ ገቢ የተሰበሰበ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የተገኘው ገቢ የዕዱን 88 ነጥብ 6 በመቶ መሆኑን አንስተው፥ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ80 በመቶ ብልጫ አለው ብለዋል።
የክልሉን ወጪ በገቢ ለመሸፈን በተሰራው ስራም 64 በመቶ በላይ የሚሆነውን መሸፈን መቻሉን አስታውቀዋል።
በቀጣይም ከደረሰኝ አሰጣጥ ጋር ተያይዞ የሚታዩ ጉድለቶችን ለመቅረፍ የአስተምሮና የግብር ህግ ማስከበር ሥራዎች ላይ በተቀናጀ መልኩ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በግማሽ በጀት ዓመቱ የታዩ ክፍተቶችን በመለየት የቀሪ ወራት ዕቅዱን ሙሉ በሙሉ ለማሳካት ይሰራልም ነው ያሉት፡፡
More Stories
እንግሊዝን ያስቆጣው የኢራን ጥቃት
በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ በሌማት ትሩፋት መርሐግብር የተሠማሩ ወጣቶች ተጠቃሚ እየሆኑ መምጣቸው ተገለጸ።
ኢራን ላይ እየተካሄደ የሚገኘው ወታደራዊ ዘመቻ …