ኢትዮጵያ በቀጣናው ውስጥ የኢኮኖሚ ውህደትን ለማሳደግ ቁርጠኛ ናት ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዎን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ገለፁ፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዎን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) በአውሮፓ የውጭ ጉዳይ አገልግሎት የፖለቲካ ጉዳዮች ምክትል ዋና ፀሐፊ ኡሎፍ ስኩግን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የአውሮፓ ሕብረት እና አባል አገሮቹ የኢትዮጵያ አስተማማኝ አጋሮች መሆናቸውን ትኩረት ሰጥተው በመግለጽ፣ ግንኙነቱን በጋራ ዕሴቶች እና ተስፋዎች ላይ የተመሰረተ ወሳኝ አጋርነት መሆኑን አንስተዋል።
ኢትዮጵያ በቀጣናው ውስጥ ኢኮኖሚያዊ ውህደትን ለማሳደግ ያላትን ቁርጠኝነት የገለፁት ሚኒስትሩ፣ እንቅስቃሴው ከአውሮፓ ሕብረት “Global Gateway initiative” ጋር የሚጣጣም መሆኑን ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ እየተከናወነ ያለው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ የፈጠረውን ምቹ የኢንቨስትመንት ዕድል በመጠቀም የአውሮፓ ኩባንያዎች በኢንቨስትመንት ዘርፎች የበለጠ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
ምክትል ዋና ፀሐፊው ኡሎፍ ስኩግ በበኩላቸው፤ በኢትዮጵያ እና በአውሮፓ ሕብረት መካከል ያለውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት ዳግም አረጋግጠዋል።
የአውሮፓ ሕብረት ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች የሚያደርገውን ድጋፍ አንስተው፤ ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. በ2027 የኮፕ32 አስተናጋጅ ሆና በመመረጧ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።
ሕብረቱ ኢትዮጵያ እያካሄደቻቸው ለሚገኙ እንቅስቃሴዎች እና ወደፊት ለሚኖሯት የልማት ውጥኖች ለመተባበር ዝግጁ መሆኑንም ምክትል ዋና ፀሐፊው ገልጸዋል።
ውይይቱ በተጨማሪ የቀጣናው ሰላም እና ደኀንነትን ያካተተ ሲሆን፣ ሁለቱም ወገኖች በጋራ ጥቅም ላይ በሚያተኩሩ ጉዳዮች አብረው ለመሥራት ተስማምተዋል።
More Stories
ዜጎች በመልዕክት መላላኪያ አማራጮች በሚፈጸሙ የሳይበር ጥቃቶች ተጋላጭ እንዳይሆኑ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡-የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር
በሸካ ዞን አስተማማኝና ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ እና የህግ የበላይነትን ለማስከበር ያለመ ዞናዊ የፀጥታ ግብረ ኃይል የምክክር መድረክ በቴፒ ከተማ ተካሄደ
ክልላዊ የተቀናጀ የማኅበረሰብ አቀፍ ተፋሰስ ልማት ማብሰሪያ ፕሮግራም በመካሄድ ላይ ይገኛል።