February 4, 2026

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የብልጽግና ፓርቲ የ6 ወራት አፈጻጸም ግምገማ በሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ ነው

ማሻ፣ ጥር 06/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍኤም 103.8) የብልጽግና ፓርቲ የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት የፓርቲ ስራዎች አፈጻጸም የግምገማ መድረክ በሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንትና የፓርቲው ዋና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ እና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰውን (ዶ/ር) ከሁሉም ክልሎች እና ከሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ የፓርቲ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በአቶ አደም ፋራህ የተመራ የአመራሮች ቡድን ሆሳዕና ከተማ ከሚካሄደው የፓርቲው የስድስት ወራት አፈጻጸም ግምገማ መድረክ አስቀድሞ በትናንትናው ዕለት በክልሉ ምስራቅ ጉራጌ እና ስልጤ ዞኖች የተለያዩ የልማት ስራዎችን ጎብኝቷል፡፡

በዚህም አመራሮቹ በቡታጅራ ከተማ የአቮካዶ ዝርያ ማሻሻያ ማዕከል፣ የወንዝ ዳር ፕሮጀክት፣ ቀሸት ንብ ማነብ ስራ ማህበር እና ደስታ ጋርመንትን ምልከታ አድርገዋል።

እንዲሁም በወራቤ ከተማ በመንግሥትና በባለሀብቶች ቅንጅት በ1 ሺህ ሄክታር ላይ በፍጥነት እየለማ የሚገኘውን የሶጃት (ንጋት) የኢንዱስትሪ ማዕከል ያለበትን ደረጃ መመልከታቸው ይታወሳል ሲል ኤፍ ኤም ሲ ዘግቧል