ማሻ፣ ጥር 06/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍኤም 103.8) 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ስብሰባውን ነገ ይካሄዳል።
ምክር ቤቱ በነገ ስብሰባው በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት እና በሕዝባዊት ሪፐብሊክ ቻይና መንግሥት መካከል የተደረገውን የወንጀል ጉዳዮች የጋራ የሕግ ትብብር ስምምነት ረቂቅ አዋጅ እና በሁለቱ መንግሥታት መካከል የተደረገውን ፍርደኞችን የማስተላለፍ ስምምነት ረቂቅ አዋጅ አስመልክቶ የሕግ እና ፍትሕ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀርበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ ረቂቅ አዋጁቹን ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
እንዲሁም ምክር ቤቱ ፣ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት እና በብራዚል ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ መንግሥት መካከል የተደረገውን ፍርደኞችን የማስተላለፍ ስምምነት ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የሕግ እና ፍትሕ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀርበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ ረቂቅ አዋጁን ያፀድቃል ተብሎም ይጠበቃል።
በተያያዘም በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት እና በደቡብ አፍሪካ ሪፐብሊክ መንግሥት መካከል የተደረገውን በወንጀል የሚፈለጉ ሰዎችን አሳልፎ የመስጠት ስምምነት ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የሕግ እና ፍትሕ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀርበውን ሪፖርትና ውሳኔ ሀሳብ መርምሮ ረቂቅ አዋጁን የሚያፀድቅ ይሆናል።
በተጨማሪም ምክር ቤቱ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በኮሪያ ኤክስፖርት – ኢምፖርት ባንክ መካከል ለሕክምና መሳሪያዎች አቅርቦት ፕሮጀክት ምዕራፍ 2 ማስፈጸሚያ የተደረገውን የብድር ስምምነት ረቂቅ አዋጅ እና የሕብረት ሥራ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ለሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች የሚመራ ይሆናል
More Stories
ዜጎች በመልዕክት መላላኪያ አማራጮች በሚፈጸሙ የሳይበር ጥቃቶች ተጋላጭ እንዳይሆኑ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡-የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር
በሸካ ዞን አስተማማኝና ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ እና የህግ የበላይነትን ለማስከበር ያለመ ዞናዊ የፀጥታ ግብረ ኃይል የምክክር መድረክ በቴፒ ከተማ ተካሄደ
ክልላዊ የተቀናጀ የማኅበረሰብ አቀፍ ተፋሰስ ልማት ማብሰሪያ ፕሮግራም በመካሄድ ላይ ይገኛል።