ማሻ፣ ጥር 04/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍኤም 103.8) የብልፅግና ፓርቲ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ሲያካሂድ የነበረውን የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወር የእቅድ አፈፃፀም ግምገማ አጠናቋል።
በማጠቃለያ መድረኩ የብልፅግና ፓርቲ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ሃላፊ ሚኒስትር ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) እንደገለፁት የፓርቲውን ዕሳቤዎች፤ ያስመዘገባቸውን ድሎች እንዲሁም ትልሞች ሁሉንም የሚዲያና የኮሚኒኬሽን አማራጮች በመጠቀም ለህዝብ የማሳወቅና ግንዛቤ የመፍጠር ተግባራት በላቀ ሁኔታ አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል።
በቅድመ ምርጫ፣ በምርጫ ዕለት እንዲሁም በድህረ ምርጫ ወቅት ትክክለኛ እና ፈጣን መረጃዎችን ለሕዝብ በማድረስ ለአገራችን የዴሞክራሲ ማበብ ጉልህ ድርሻ ሊወጡ ይገባል ብለዋል።
የምርጫ ምህዳሩን ለማወክ ሊሰነዘሩ የሚችሉ አፍራሽ አስተሳሰቦችን በአጀንዳና በመረጃ የበላይነት በመያዝ ምርጫው ነጻ፣ ፍትሃዊ፣ ሰላማዊና በሕዝብ ዘንድ ተዓማኒነት ያለው ሆኖ እንዲጠናቀቅ የሚዲያና ኮሚኒኬሽን ዘርፍ በግንባር ቀደምነት ሚና እንዲወጣም አሳስበዋል።
ሁሉንም የኮሚኒኬሽን፣ የሚዲያ አማራጮችንና የህዝብ ግንኙነት ስራዎችን አቀናጅቶ የመጠቀም እንዲሁም የአቅም ግንባታ ስራ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚባም ገልፀዋል።
ዘርፉ ባለፉት ሁለት ቀናት ሲያካሂድ የነበረውን የእቅድ አፈፃፀም ግምገማ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ መጠናቀቁን ከክልሉ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ድረ ገጽ የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
More Stories
ዜጎች በመልዕክት መላላኪያ አማራጮች በሚፈጸሙ የሳይበር ጥቃቶች ተጋላጭ እንዳይሆኑ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡-የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር
በሸካ ዞን አስተማማኝና ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ እና የህግ የበላይነትን ለማስከበር ያለመ ዞናዊ የፀጥታ ግብረ ኃይል የምክክር መድረክ በቴፒ ከተማ ተካሄደ
ክልላዊ የተቀናጀ የማኅበረሰብ አቀፍ ተፋሰስ ልማት ማብሰሪያ ፕሮግራም በመካሄድ ላይ ይገኛል።