ማሻ፣ ጥር 01/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍኤም 103.8) ባለፈው ረቡዕ በስኮትላንድ ሰሜናዊ ምስራቅ ዓለም አቀፍ የባህር ጠረፍ የተያዘችው መርከብ ‘ማሪኔራ’ ተብላ የምትጠራ ሲሆን፥ ማዕቀብ የተጣለበትን የቬኒዝዌላ የነዳጅ ዘይት የጫነች ናት በሚል በአሜሪካ የአውሮፓ ዕዝ ጦር መያዟ ይታወሳል።
28 አባላት ያሏት መርከቧ ሁለቱ ሩሲያውያን ሲሆኑ፥ 17 ዩክሬናውያን፣ 3 የጆርጂያ እና 3 የህንድ ዜጎች ይገኙበታል።
የሩሲያ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤትም የትራምፕ አስተዳደር ዜጎቹን ስለለቀቀለት ምስጋናውን አቅርቧል።
ሚኒስቴሩ በትናንትናው ዕለት የመርከቧ መያዝ አግባብነት የሌለውና በአካባቢው ዳግም ውጥረትን የሚያነግስ ነው ሲል ማስጠንቀቁን አር ቲ በዘገባው አስታውሷል።
More Stories
እንግሊዝን ያስቆጣው የኢራን ጥቃት
በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ በሌማት ትሩፋት መርሐግብር የተሠማሩ ወጣቶች ተጠቃሚ እየሆኑ መምጣቸው ተገለጸ።
ኢራን ላይ እየተካሄደ የሚገኘው ወታደራዊ ዘመቻ …