February 4, 2026

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ሴቶች ለሠላም ግንባታና ዴሞክራሲያዊ ባህል መስፈን የሚያደርጉትን ሚና ወደ ፊት ማምጣት እንዳለባቸው ተጠየቀ

ማሻ፣ ታህሳስ 24/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍኤም 103.8) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያዊ ህዝቦች ክልል የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቦንጋ ማዕከል “ለዴሞክራሲያዊ ባህል ግንባታ የሴቶች ሚና” በሚል መሪ ቃል የንቅናቄ ማጠቃለያ መድረክ አካኺዴል።

በመድረኩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የሴቶች ክንፍ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሠብለ ፀጋ: ከብልፅግና ፓርቲ እሳቤዎች አንዱ ዘላቂ ሠላምን በንግግርና በድርድር ማስፈን በመሆኑ እኛ ሴቶች ለተግባራዊነቱ መተግጋት ይጠበቅብናል ብለዋል።

የፓርቲያችን ፕሬዝዳንት ክቡር ዶክተር አብይ አህመድ “የብልፅግና ዘር ሀሳብ ነው” እንዳሉት ሃሳቦች የሚንሸራሸሩበትና ወደ መግባባት በሚመጡበት ሁኔታ ሀገር በቀል እውቀቶች የበላይነትን እንዲይዙ ሴቶች ጠንክረው መስራት እንዳለባቸውም ወ/ሮ ሠብለ አሳስበዋል።

ብልጽግና ፓርቲ የርዕዮተ ዓለም አድማሱን ያላቀ እና በመደመር እሳቤ በመመራት የፖለቲካ ምህዳር ማስፋፋቱ ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ የማይተካ ሚና እየተጫወተ ይገኛል ብለው እኛ ሴቶች በሚንታወቅበት መንገድ ለሀገር አንድነት ሌት ተቀን ሊንሰራ ይገባል ብለዋል።

በየጊዜ የሚስተዋሉ የሠላም እጦት ሴቶችን በመጀመሪያ ደረጃ ይጎዳል ያሉት ኃላፊዋ በክልላችንና በአካባቢያችን ብሎም በሀገራችን ሠላም እንዲሰፍን በሁሉም ዞኖቻችን በተዘጋጀው “የቡና ጠጡ” ውይይቶች ላይ የነቃ ተሳትፎ በማድረግ ልዩነታችንን የሚያጠብ አብሮነታችንና እህታማማችነት እሴት እያጎለበቱ እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።

በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ አስተባባሪነት 200 ብር ለእናቴ ንቅናቄ 2.1 ሚልዮን ብር ተሰብስቦ ለተለያዩ ሴቶች የስራ ዕድል የተፈጠረ ሲሆን በቀጣይም የሴቶችን ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት እውን ለማድረግ እንደሚሰሩም ወ/ሮ ሠብለ ተናግረዋል።

በማጠቃለያ መድረኩ የተለያዩ የክልሉ መንግስት የስራ ኃላፊዎች የተሳተፉት ሲሆን የባህላዊ ጨዋታዎች፣ ባህላዊ ምግቦች አውደርዕይና ጥያቄና መልስ እንዲሁም የ 5 ሚልዮን ኢትዮ ኮደርስ ላይ ግንዛቤ ማስጨበጫ ተሰጥውበት ተጠናቋል