ማሻ፣ ታህሳስ 24/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍኤም 103.8) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የ2018 በጀት ዓመት የማኅበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን (CBHI) አፈጻጸም ግምገማ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
የክልሉ መንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ፍቅሬ አማን በመድረኩ መክፈቻ ላይ እንደገለጹት፤ የዜጎችን ማህበራዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ በየደረጃው ያለው አመራር ቁርጠኝነት ሊጠናከር ይገባል።
ክልሉ በማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አፈጻጸም እንደ ሀገር የተሻለ ውጤት ሲያስመዘግብ መቆየቱ ተገልጿል።
ውጤቱን በዘላቂነት ለማስቀጠል ክፍተቶች መኖራቸውን የጠቆሙት አቶ ፍቅሬ፤ በተለይም በዞኖች መካከል ያለውን የአፈጻጸም ልዩነት ለማጥበብ በትኩረት መሥራት እንደሚገባ አሳስበዋል።
የማህበራዊ ልማት ስራዎች የብልፅግና ፓርቲ ሰው ተኮር እሳቤ ነጸብራቅ በመሆናቸው፤ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ርብርብ ይደረጋል።
በበጀት ዓመቱ የመድኃኒት አቅርቦትና የአገልግሎት አሰጣጥ ላይ መሻሻሎች መታየታቸው ተገልጿል።
መድረኩ በቀጣይ አጭር ጊዜ ውስጥ የአዲስ አባል ምዝገባ እና የነባር አባላት ዕድሳትን ለማጠናቀቅ የጋራ መግባባት በመፍጠር ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል። መረጃው የክልሉ ኮሚዩኒኬሽን ነው
More Stories
ዜጎች በመልዕክት መላላኪያ አማራጮች በሚፈጸሙ የሳይበር ጥቃቶች ተጋላጭ እንዳይሆኑ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡-የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር
በሸካ ዞን አስተማማኝና ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ እና የህግ የበላይነትን ለማስከበር ያለመ ዞናዊ የፀጥታ ግብረ ኃይል የምክክር መድረክ በቴፒ ከተማ ተካሄደ
ክልላዊ የተቀናጀ የማኅበረሰብ አቀፍ ተፋሰስ ልማት ማብሰሪያ ፕሮግራም በመካሄድ ላይ ይገኛል።