February 4, 2026

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ሳውዲንና ኤሜሬቶችን ያቃቃረው የየመን ውጥረት

ሳውዲ አረቢያ ፤አረብ ኤሚሬቶች የየመን  ገንጣይ ቡድኖችን እየደገፈች ነው በሚል ወቅሳለች።

ይህን ተከቶልም አቡ ዳቢ በ24  ሰዓታት ውስጥ ከአካባቢው እንድትወጣ በፕሬዚዳንታዊ አመራሩ ምክር ቤቱ (እውቅና ያለው መንግስት)ተነግሯታል።

ሪያድም የ’ፒ ኤል ሲ’ን ሀሳብ ተከትላ አቡ ዳቢ የደቡባዊ ሽግግር ምክር ቤቱ (ኤስ ቲ ሲ)ን በጦር መሳሪያ እየደገፈች ነው በሚል ከሳለች።

የመን በሁቲዎች ፣በደቡባዊ ተገንጣዮች እና በፕሬዚዳንታዊ አመራር ምክር ቤቱ ሀይሎች ተከፍላ እየታመሰች ይገኛል።

ኤሚሬቶችም በየመን የምታደርገውን ፀረ-ሽብር ዘመቻ ማቆሟን እና ከየመን የመውጣቷን ነገር ይፋ አድርጋለች።

ኤስ ቲ ሲ ሳውዲ አረቢያ ሁቲዎችን ከማጥፍት ይልቅ ትኩረቷን ደቡባዊ የመን ላይ ማድረጓ ቀጠናው እንዳይረጋጋ ያደርጋል በሚል ወቅሷል።

ቡድኑ ከሳውዲ መራሹ ጥምረት እና በመንግስታቱ ድርጅት እውቅና ከተሰጠው መንግስት ጎን ቆሞ አንሳራላሆችን (ሁቲዎችን) መውጋቱ ይታወሳል።

በሳውዲ የሚመራው ሀይል በደቡባዊ የመን ሙካላ ወደብ የአየር ጥቃት ማድረሱ ደግሞ ውጥረቱን ቀጠናዊ አድርጎታል።

በድንበር አካባቢ የደህንነት ስጋት ያለባት ሪያድ አካባቢውን በጦር የማስታገስ ውጥን እንዳላትም ተነግሯል።

በሌላ በኩል በየመን ጉዳይ ላይ አንድ አቋም የነበራቸው ሁለቱ ቁልፍ የገልፍ ምክር ቤት አባላት ሳውዲ እና ኤሚሬቶች ፖለቲካዊ መቃቃር ውስጥ ገብተዋል።

ዘገባው የአልጀዚራ ነው።