ዓለም አቀፍ የፀረ-ተዋሲያን መድኃኒቶች በጀርሞች መለመድ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሳምንት”አሁን እንተግብር፣ ዛሬን እንጠብቅ፣ የወደፊታችንን እናረጋግጥ” በሚል መሪ ቃል በቦንጋ ከተማ እየተካኸደ ነው።
በመድረኩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ተማም ዓለም አቀፍ የፀረ-ተዋሲያን መድኃኒቶች በጀርሞች መለመድ በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ የጤና ስጋት እየሆነ ስለመጣ የግንዛቤ ማስጨበጫ ንቅናቄው በተቀናጀ መልኩ ወደ ህብረተሰቡ መድረስ አለበት ብለዋል።
የፀረ-ተዋሲያን መድኃኒቶች በጀርሞች መለመድ አግባብነት በሌለው መድኃኒት አጠቃቀም ሥርዓት ይገለጻል ያሉት የቢሮ ኃላፊው: ህብረተሰቡ ለሚታዩ የህመም ምልክቶች ሁሉ ያለ ሀኪም ትዕዛዝ መውሰድ መድኃኒቶቹ በጀርሞች መለመድ ከዋነኞቹ መንስኤዎች አንዱ መሆኑን ጠቁመዋል።
የታዘዙትን መዲኃኒቶች በአግባቡ ያለመጭረስና ከዶዝ በላይ መውሰድም ጀርሞቹ ፀረ-ተዋሲያን መዲኃኒቶችን እንዲላመዱ ያደርጋል ብለው የመዲኃኒት አጠቃቀም ሥርዓታችን ደካማ መሆንና አዳዲስ ፀረ-ተዋሲያን መዲኃኒቶች በዓለም ደረጃ እየተመረቱ ያለመሆን ጫናውን ከፍ እንዳደረገ ገልጸዋል።
የአካባቢ ንፅህናን ማረጋገጥና ሀገር በቀል እውቀቶችን በዚሁ ዘርፍ ከፍ ማድረግ እንደ ሀገር የመፍትሔ አቅጣጫ ነው ያሉት አቶ ኢብራሒም: የግንዛቤ ማስጨበጫ ንቅናቄውን በቅንጅት በመስራት ዜጎች ለጤንነታቸው ትርጉም እንዲሰጡ እስከ መንደሮች ድረስ ሊመራ ይገባል ብለዋል።
የመወያያ መነሻ ሰነድ በመድኃኒትና ህክምና መሣሪያ አስተደር ዳይሬክተር አቶ አበበ ከበደ በኩል እየቀረበ ሲሆን: የርዕሰ መስተዳድሩ የህግና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች አማካሪ አቶ ዳግም ዳንኤልን ጨምሮ የክልሉ መንግስት የስራ ኃላፊዎችና ሌሎች ተጠሪ ተቋማት እየተሳተፉ ይገኛሉ።
More Stories
ዜጎች በመልዕክት መላላኪያ አማራጮች በሚፈጸሙ የሳይበር ጥቃቶች ተጋላጭ እንዳይሆኑ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡-የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር
በሸካ ዞን አስተማማኝና ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ እና የህግ የበላይነትን ለማስከበር ያለመ ዞናዊ የፀጥታ ግብረ ኃይል የምክክር መድረክ በቴፒ ከተማ ተካሄደ
ክልላዊ የተቀናጀ የማኅበረሰብ አቀፍ ተፋሰስ ልማት ማብሰሪያ ፕሮግራም በመካሄድ ላይ ይገኛል።