February 4, 2026

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የህዝቡን ሁሉን አቀፍ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነትን ዕውን ለማድረግ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ የክልል ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ገነት መኩሪያ ገለፁ።

ማሻ ፣ የታሕሳስ 17/2018 (ማሻ ኤፍ ኤም)‌‌‌‌‎ ‌‌‌‌‌‌‌‎”የጉባ ብስራቶች የመደመር መንግስት ትሩፋቶች” በሚል መሪ ቃል በሸካ ዞን ማሻ ከተማ በነገው ዕለት የህዝብ ውይይት መድረክ እንደሚካሄድም ጠቁመዋል ።

በዚህ የውይይት መድረክ ላይ ከ4መቶ በላይ ባለድርሻ አካላት ከሁሉም ማህበራዊ መሰረት ይሳተፋሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን የመድረኩን ቅድመ ዝግጅት በተመለከተ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት አድርገዋል ።

በዚህ የቅድመ ዝግጅት ውይይት ላይ የተገኙት የክልል ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ገነት መኩሪያ
የጉባ ብስራቶች የመደመር መንግስት ትሩፋቶች” በሚል መሪ ቃል
የህዝቡን ሁሉን አቀፍ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነትን ዕውን ለማድረግ ያለመ ህዝባዊ ውይይት የሚካሄድ መሆኑን ገልፀዋል ።

በመድረኩ ላይ ወቅታዊ የልማት፣መልካም አስተዳደርና ሰላም ጉዳዮች ላይ ከህዝብ ጋር ውይይት በማድረግ ጠንካራ ጎን በማስቀጠል ድክመቶችን ማረም እንደሚገባ ገልጸዋል ።

የህዝቡን የመልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄ ለመመለስ የተደረጉ ውጤታማ ስራዎችን በመለየት እንዲሁም ምላሽ ያላገኙ ጉዳዮችን ለይተው በማውጣት ቀጣይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ በሰፊው ውይይት ማድረግ እንደሚገባ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

የሸካ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ሀላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አለማየሁ አለሙ መንግስት ከህዝብ ጋር ተቀራርቦ የውይይት መድረክ በመፍጠር የህዝብ ጥያቄ በማድመጥ ምላሽ ለመስጠት የሚያደርገው እንቅስቃሴ የሚበረታታ መሆኑን በመግለፅ ይህን በማጠናከር ውጤታማ ለውጥ ለማምጣት ትኩረት ሰጥተን እየሰራን ነው ብለዋል።

በመደመር መንግስት የተሰሩ ጠንካራ ስራዎችንና የጉባ ብስራቶችን ለህዝብ ግልጽ ለማድረግ የሚደረገው የህዝብ ውይይት መድረክ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው በመግለፅ ለህዝቡ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የተጀመረውን የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ ትኩረት ሰጥቶ መንግስት እንደሚሰራም ጠቁመዋል ።

የማሻ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አንዱአለም ጌታቸው የከተማ ነዋሪዎችን ልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኙ እንዲሁም የከተማ ሰላም ለማስጠበቅ የከተማ አቀፍ የህዝብ ውይይት እየተደረገ መቆየቱን በመግለፅ ለሚደረገው የህዝብ ውይይት አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅት መደረጉን ጠቁመዋል።

በሚካሄደው የህዝብ ውይይት መድረክ ላይ ከ4መቶ በላይ ከሁሉም ማህበራዊ መሰረት የተወጣጡ አካላት የሚሳተፉ መሆናቸውን በመግለፅ የሀገር ሽማግሌዎች ፣የሀይማኖት አባቶች፣ወጣቶች፣ሴቶች ፣ታዋቂ ግለሰቦች ፣ተፎካካሪ ፓርቲዎች ፣የከተማ መንግስት ሰራተኞችና ለሎች ባለድርሻ አካላት ይሳተፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጸዋል።

በመጨረሻም በማሻ ከተማ ውስጥ እየተገነባ ያለው የውሃ ፕሮጀክትና ለሎች የልማት እንቅስቃሴዎችን ጉብኝት በማድረግ የህዝብ ውይይት መድረክ ቅድመ ዝግጅት ያለበት ደረጃ ላይ የተደረገው ግምገማ ተጠናቋል ።